የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመመዝገብ የሚያስችል ድረ-ገፅ በሥራ ላይ አዋለ

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር (ኢአማ) በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከታተል እና ለመመዝገብ የሚያስችል sojethiopia.org የተሰኘ ድረ-ገፅ ወይም ፖርታል አዘጋጅቶ ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም በሥራ ላይ አዋለ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) ድጋፍ በኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር ተዘጋጅቶ ስራ ላይ የዋለው ይህ ፖርታል በመጀመሪያው ምዕራፍ በሶስት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ ፣ ኦሮምኛ እና እንግሊዝኛ ተዘጋጅቷል፡፡
ማኀበሩ በማዶ ሆቴል ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም እንደገለፀው ድረ-ገፁ በጋዜጠኞች እና በብዙሃን መገናኛ ተቋማት ላይ የሚደርሱ እንደግድያ ፤ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ፤ የመስሪያ ቦታ ማሸግ እና ፈቃድ ክልከላ ፤ ፆታዊ ጥቃት ፤ እስር ፤ እገታ ፤በማህበራዊ ሚድያ እና በሌሎችም መንገዶች የሚደረጉ ማንቋሸሽ ፣ ዘለፋ ፣ ስም ማጥፋት ፣ እና የመሳሰሉትን በመመዝገብ ፣ በማጣራት እና ለቀጣይ ውትወታ ስራዎች ግብዐት በመሰብሰብ መገናኛ ብዙሃን ነፃነታቸው ተጠብቆ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደት ላይ የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡
sojethiopia.org ጋዜጠኞች ስራቸውን በሚሰሩበት ወቅት የሚደርስባቸውን ማዋከብ እና የመሳሰሉት ክስተቶች ሲያጋጥም ከመከታተል እና ከመመዝገብ በተጨማሪ እና በተለየ ሁኔታ ፤ ሴት ጋዜጠኞች በስራ ቦታቸውም ሆነ በጋዜጠኝነት ጉዞአቸው ላይ የሚደርሱባቸው ፆታዊ ጥቃቶችን ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ የሚመዘግብ እና የመፍትሄ ሒደቶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የሚያመቻችበት ማዕቀፍ ነው፡፡
ስለኢአማ
የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር (Editors Guild of Ethiopia) በኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 4527 ተመዝግቦ የተመሰረተ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቭዥን ፣ የጋዜጣ ፣ የሬዲዮ እና የበይነ-መረብ ዜና አርታኢያንን በአባልነት ያቀፈ ማህበር ነው፡፡ የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ደህንነትን የተመለከቱ ጉዳዮች የማህበሩ አንዱ እና ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ኢአማ በጋዜጠኞች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ከሰብአዊ መብት ጥሰት ባሻገር በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያደርስ ያምናል፡፡
ስለ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (UNESCO) በኦስትሪያ ቪየና በህዳር 2012 (እኤአ) በተባበሩት መንግስታት የስራ አስፈፃሚ ቦርድ የፀደቀውን የጋዜጠኞች ደህንነት የተመለከተውን UN Plan of Action on the Safety of Journalists and the Issue of Impunity በመላው አለም እንዲያስተባብር ኃላፊነት የተሰጠው ድርጅት ነው፡፡
SourceEGE

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe