የኢትዮጵያ አየር መንገድ፥ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳላጓጓዘ አስታወቀ

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአፍሪካ ግዙፉ እና ግንባር ቀደሙ አየር መንገድ ወትግራይ እንዲሁም ወደሌሎች ቦታዎች መሳሪያ እያዘዋወረ ነው በሚል ስሙ ተነስቷል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (OLF) ይፋዊ የፌስቡክ ገፅም አየር መንገዱ ወደ መቐለ፣ ሃዋሳ፣ ኮምቦልቻ የጦር መሳሪያ እያዘዋወረ ነው ሲል በይፋ ፅፏል፤አየር መንገዱን ሎጅስቲክስ በማመላለስ የጦርነት ተሳታፊ እየሆነ ነው ሲል ከሷል።

ትላንት ምሽት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ ምላሽ ሰጥቷል።

ሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሳሪያ እያጓጓዘ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ መሆኑን አስረድቷል።በየትኛውም የሀገር ውስጥ ሆነ የውጪ በረራዎቹ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ እንዳላጓጓዘ ገልጿል።

አየር መንገድ፥ “ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወደ የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል አላጓጓዝኩም፤ እንዳጓጉዝም አልተጠየኩም” ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አንጋፋና ፓን አፍሪካዊ አየር መንገድ መሆኑን ፣ ለአፍሪካውያን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በግንባር ቀደምነት ላለፉት 75 ዓመታት አህጉሩን ሲያገለግል መቆየቱን በዚህም አየር መንገዱ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በተቀረው ዓለምም እጅግ የሚያኮራ ስም ማፍራቱን አንስቷል።በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በሰራው ስራም ከተለያዩ ሀገራት እና መሪዎች እውቅና ለማግኘት መብቃቱን አስታውሷል።

ነገር ግን “አንዳንድ ሀላፊነት የማይሰማቸው ግለስቦች” ሀሰተኛ እና በፎቶ ሾፕ የተቀናበሩ ምስሎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በማሰራጨት የአየር መንገዱን ስም እና ዝና ለማጠልሸት የሚያደርጉት ጥረት መኖሩን ደምበኞቹ እንዲገነዘቡ አሳውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe