የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከምርጥ 200 አየር መንገዶች 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባጓጓዘው የመንገደኛ ብዛት ከምርጥ 200 አየር መንገዶች 20ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን አለም አቀፍ የትራንስፖርት ማህበር አስታውቋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ስፍራ ያገኘው ከ16 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች በማጓጓዝ መሆኑን አየር መንገዱ ማህበሩን ዋቢ አድርጎ ካገኘው መረጃ መረዳት ተችሏል።

በዚህ የደረጃ መስፈርት መሰረት በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠው የኤምሬትስ አየር መንገድ ሲሆን 78 ሚሊዮን746 ሺህ መንገደኞችን አጓጉዟል።በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው የአየርላንዱ ራይኔይር በበበኩሉ 64 ሚሊዮን 928 ሺህ መንገደኞችን ማጓጓዙ ተገልጿል።በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጠው የኳታር አየር መንገድ 57 ሚሊዮን 171 ሺህ መንገደኞችን ማጓጓዙን ከድረ-ገፁ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

የኮሮናቫይረስ ክፉኛ ከጎዳቸው ዘርፎች መካከል የአየር ትራንስፖርት አንዱ ሲሆን፤ በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ አየር መንገዶች ሠራተኞቻቸውን ከመቀነስ አንስቶ ከበረራ ውጪ አስኪሆኑ ድረስ ጉዳት አድርሷል።በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ አየር መንገዶች በባለፈው አመት ቀውስ ውስጥ የገቡና ሥራ ለማቆም የተገደዱ ያሉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ጭነቶችን በማመላለስ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማለፍ እንደቻለ ተነግሯል።

 

Source[BBC]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe