በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ምርጥ ብራንድ ያላቸው ድርጅቶችንና ምርቶችን በማወዳደር ይፋ የሚያደርገው ብራንድ አፍሪካ 2020 መፅሔት ተቋማቱን ብቃትና ተቀባይነት በመመዘን አስሩን ድርጅቶች ይፋ አድርጓል፡፡
Read also:የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ አስተናጋጆች ለመስጠት የወሰነው የቋንቋ ፈተና ተቃውሞ ገጠመው
በአፍሪካ ከሚገኙ አስር ምርጥ ብራንድ ያላቸው ድርጅቶች መሀከል አራቱ የደቡቡ አፍሪካ ሲሆኑ ሶስቱ የናይጄሪያ ናቸው፤ ሁለቱ የኢትዮጵያ /የኢትዮጵያ አየር መንገድና አንበሳ ጫማ / አንዱ የታንዛኒያ ነው፡፡ የሚገርመው ከአስሩ የአፍሪካ ብራንድ ድርጅቶች መሀከል ዘጠኙ ባለቤትነት የተያዘው አፍሪካውያን ባልሆኑ ባለሀብቶች ሲሆን ብቸኛውና በሀገሩ ዜጎች ባለቤትነት የተያዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ ነው፡፡ እሱም በጥቂት ዓመት ውስጥ ከኢትዮጵያውያን እጅ ለማውጣት እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡