የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ተቃውሞ ገጠመው

በቅርቡ በሚካሄደው አገራዊ ምክክር መድረኩ የሚጠበቀው ውጤት በአዋጁ አለመመላከቱ ተቃውሞ ገጠመው፤

በሕዝብ ተወካዮች የምክር ቤት የህግ፤ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከአገራዊ ምክክር መድረኩ የሚጠበቀው ውጤት በአዋጁ ሊመላከት እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ዙሪያ ከአስረጂዎች ጋር በተወያየበት ወቅት ነው፡፡

በተዘረዘረው የኮሚሽኑ አላማ ውስጥ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመቅረፍ የሚሰሩ ስራዎችን በማካተት በምክክር መድረኩ የሚጠበቀው ውጤት በአዋጁ ሊካተት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ደንብ የማውጣት ስልጣን፣ የዕጩዎች ጥቆማ እና ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው በህግ የሚጠየቁ ክልከላዎችን በአዋጅ ስለማስቀመጥ እንዲሁም ከክልሎች ጋር ተቀናጅቶ ስለመስራትም ሆነ በክልሎች ቅርንጫፎችን ስለመክፈት በአዋጁ በዝርዝር ሊቀመጥ እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አመላክቷል፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄ እና አስተያየት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ሃገራዊ መግባባት እንዲፈጠር ኮሚሽኑ የበኩሉን ድርሻ አካታች በሆነ መልኩ በመርህ ላይ የተመሰረቱ ስራዎችን ሊሰራ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም ክልሎችን በሚመለከት ለተነሱት ምክረ ሃሳቦች ከአሁን ቀድሞ ማወቅ ስለማይቻል በቀጣይ በአዋጁ በግልፅ እንደሚመላከትና ቅርንጫፎች መክፈትን አስመልክቶ በኮሚሽኑ አቅም ሊወሰን እንደሚችል ማማላከታቸውን የዘገባው ዜና ፖርላማ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe