የኢትዮጵያ ወዳጅ ሪታ ፓንክረስት አረፉ!

የታዋቂው የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክረስት ባለቤት ሪታ ፓንክረስት በ92 አመታቸው አረፉ፡፡ ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትናንት ባወጣው የሐዘን መግለጫ እንዳመለከተው የታዋቂው ኢትዮጵያ ወዳጅና የታሪክ ምሁር ሪቻርድ ፓንክረስት ባለቤት ሪታ ፓንክረስት አርፈዋል፡፡

እ.አ.አ በ1927 ሮማንያ የተወለዱት ሪታ በ1938 (እ.አ.አ) ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ እንግሊዝ ሄደዋል፡፡

‹ፐርሴ የሴቶች ትምህርት ቤት› ትምህርታቸውን የተከታተሉት ሪታ በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ ቋንቋን (ፈረንሳይኛና ራሽያኛ) ተምረዋል፡፡ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በ1948 ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለዋል፡፡

በ1956 (እ.አ.አ) አዲስ አበባ ከባለቤታቸው ሪቻርድ ፓንክረስት ጋር ተገናኙ፡፡ በአዲስ አበባ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍ ሥራ ጀመሩ፡፡ በዓመቱም ከሪቻርድ ፓክረስት ጋር ጋብቻ መሠረቱ፡፡ አሉላ እና ሄለን የተባሉ ሁለት ልጆችንም አፈሩ፡፡

አብዛኛውን በቤተ መጻሕፍት ዘርፍ በመሥራት ያሳለፉት ሪታ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ (አዲስ አበባ) ዩኒቨርሲቲ ለአስርት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የንጉሣዊው ሥርዓት ከተወገደ በኋላ የነበረው ሁኔታ ምቹ ባለመሆኑ በ1976 (እ.አ.አ) ወደ ሎንዶን ተመልሰዋል፡፡ በዚያም በሎንዶን ፖሊቴክኒክ የቤተ መጻሕፍ ኃላፊ ሆነዋል፤ ከ11 ዓመታት ቆይታ በኋላም ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰቡ ተመልሷል፡፡

ልጆቻቸውን በእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች ጥለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ሪታ ፓንክረስት የቤተ መጻሕፍ አማካሪ፣ የመጻሕፍትና የመመረቂያ ጥናቶች አርታኢ በመሆን ሠርተዋል፡፡ በሌሎች የበጎ ፈቃድ ተግባራትና ኃላፊነቶችም ኢትዮጵያን አገልግለዋል፡፡

የተለያዩ ጥናቶችንም ለንባብ አብቅተዋል ‹‹የኢትዮጵያ ቅሪቶችና ታሪካችን›› (Ethiopian Reminiscences) የሚል ትርጓሜ ያለው መጽሐፍንም ለንባብ አብቅተዋል፡

ምንጭ፡- በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe