የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የኢፌዴሪ መከላለከያ ሠራዊት ላይ የከፈተውን ጥቃት በፅኑ አወግዛሁ አለ

በተለያየ ጊዜ ህወሓት ሲያስተላልፋቸው የነበሩ የሥርዓት አልበኝነት ጥሪዎች እና በክልሉ ሕግን ተላልፎ ሲፈፅም የነበራቸው ድርጊቶች አልበቃ ብለው የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ምልክት የሆነው መከላከያ ሠራዊታችን ላይ የፈፀመው ጥቃት በፍፁም በዝምታ የሚታለፍ እንዳልሆነ እናምናለን ብሏል።
የነበረው ችግር በንግግር መፈታት ከሚችልበት ምዕራፍ አልፎ አሁን የደረሰበት ደረጃ መድረሱ በጣም አሳዝኖናል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሀገር አንድነት እና ሰላምን ለማስከበር የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በመደገፍ የኢዜማ አባላት እና አመራር ከጎኑ እንደምንሰለፍ እናሳውቃለን።
በሚወሰዱ እርምጃዎች ሰላማዊ ዜጎችን ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳይደርስባቸው አስፈላጊው ጥንቃቄ መደረግ እንደሚገባው ለማስታወስ እንወዳለን።
የትግራይ ሕዝብ የሚወሰደው እርምጃ ለሀገር አንድነት እና ሰላም ማስከበር ብቻ እንደሆነ በመረዳት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንዲቆም እንጠይቃለን።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ይህንኑ በመረዳት አብሮነታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ እና ለሰላም እና ደህንነት እንቅፋት የሚሆኑ ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች ከማድረግ ተቆጥበን አካባቢያችንን በንቃት እየጠበቅን ለሰላም እና ደህንነት መከበር ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ትብብር እንድናደርግ የአደራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe