የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE) የሚዲያ ቁጥጥርና ዳሰሳ እንደሚሰራ አሳወቀ።

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (CECOE) ባቋቋመው የሚዲያ ታዛቢ ቡድን አማካኝነት በምርጫው ወቅት የሚዲያዎችን ዘገባ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

በአምስት ሀገር አቀፍ ቋንቋዎችና ዓለም አቀፍ ቋንቋዎች መሰረት አድርጎ የተቋቋመው ቡድኑ 10 የቴሌቪዥን እንዲሁም የሬዲዮ ጣቢያዎች ላይ ቁጥጥር ያደርጋል።

የሚዲያ ቁጥጥርና ዳሰሳ ሥራው በዋናነት በምርጫ ወቅት የመገናኛ በብዙኀን ሚና ምንድን ነው የሚለውን ለመመልከት እንደሆነና ይህንን የሚገልጽ ሪፖርት ለማውጣት ዓላማ ያደረገ እንደሆነ ተጠቅሷል።

ከዚህ ቀደም በምርጫ ወቅት የሚዲያዎችን አስተዋፅኦ በተደራጀ መልኩ የሚታዘብ የሲቪክ ማኅበር አልነበረም፥ አሁን ላይ ግን የሀገር ውስጥና የውጪ ሚዲያዎችን ተሳትፎ የሚያሳይ ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርግ ነው የገለጸው።

በ The Hub ሆቴል ያለው ይህ የሚዲያ ተቆጣጣሪ ቡድንና የመቆጣጠሪያ ጣቢያ በተለዩ ሰዓቶች የሚተላለፉ 10 የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎችን ይዘቶችን ለ6 ወር ይዞ ይቆያል ተብሏል። አብዛኞቹ መንግስታዊ መሰረት ያላቸው ጣቢያዎች ናቸው።

የግልና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም የውጭ ሚዲያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ምርጫን መሰረት ያደረገ ሥራቸው የዳሰሳ ሥራ የሚሰራባቸው ይሆናል፥ ይህም በረፖርቱ የሚካተት ይሆናል ነው የተባለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe