“በግማሽ አመቱ ከ271 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገብኩ” – የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ከሰጠው አገልገሎት 271 ሚሊዮን 72 ሺህ 823 ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ።
ኢንተርፕራይዙ አምስተ ሚሊዮን 534 ሺህ 699 የትራፊክ ፍሰት በማስተናገድ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት እና ከልዩ ልዩ ገቢዎች 514 ሚሊዮን 602 ሺህ 957 ብር ከ 45 ሳንቲም ገቢ ማግኘት ችሏል።
በመጀመሪያ 6 ወራት ከታክስ በፊት 271 ሚሊዮን 72 ሺህ 823 ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን ከባለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 27 ነጥብ 8 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስታውቋል።
የኢንተርፕራይዙ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያዉ ስድስት ወራት የትርፍ አፈፃፀም ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸርም 111 በመቶ ድርሻ እንዳለው ነው የገለጸው።

