የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር በመድሐኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አከፋፋዮች ላይ የተጣለው የ2.5 በመቶ አነስተኛ የግብር ምጣኔ ቀሪ እንዲሆን ጠየቀ

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) በመድሐኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አከፋፋዮች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የተጣለው የ2.5 በመቶ አነስተኛ የግብር ምጣኔ ቀሪ እንዲሆን ጠየቀ።

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን የጅምላ አከፋፋዮች ንኡስ ዘርፍ በቅርቡ በወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017 የዝቅተኛ አማራጭ ግብር ምጣኔ ምክንያት ከፍተኛ ተጎጂ መሆናቸውን በመግለጽ ውሳኔው ቀሪ እንዲሆንለት ለገንዘብ ሚኒስቴር በላከው ደብዳቤ ጠይቋል።

ማህበሩ “ውሳኔው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የማህበሩን አባላት የሚጎዳ በመሆኑ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ” ሲል ጥቅምት 24/2018 ዓም ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄውን በደብዳቤ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ማህበር (ኢፋማ) በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው ደብዳቤ በዝርዝር ምን ይላል ?

” በቅርቡ የተከበረው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ካወጣው የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ እንደተመለከትነው አነስተኛው የግብር መጠን ከአጠቃላይ ሽያጩ 2.5 በመቶ መሆን እዳለበት ተገልጿል የዚህም ድንጋጌ መነሻ በገቢዎች ሚኒስቴር ተጠንቶ የቀረበው አማካኝ የ31 በመቶ Gross margin መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡

ሆኖም ይህ ጥናት ካለው እውነታ ጋር በፍፁም የማይጣጣም ነው፡፡

እንደሚታወቀው የመድኃኒት አከፋፋዮች አማካይ Gross margin ከ 7.5 በመቶ እስከ 10 በመቶ ሲሆን ይህንን እውነታም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀላሉ ሊያረጋግጠው የሚችለው ነው፡፡

ዘርፋችን መድሀኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በማከፋፈል ማሀበረሰቡን በማገልገል ረገድ የአንበሳውን ድርሻ የሚወጣ ሆኖ ሳለ ይህ ዉሳኔ ዘርፉን ለኪሳራ በመዳረግ የሚያቀጭጭ እና ሊያጠፋውም የሚችል ነው።

የዘርፉ መጎዳት ደግሞ በዘርፉ ዉስጥ በቀጥታ የተሰማራውን ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የመድሐኒት አቅርቦቱንም በከፍተኛ ሁኔታ በማስተጓጎል የጤናውን ዘርፍ የሚጎዳ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የባንክ ብድር፣ገበያ ከፍ ዝቅ በማለቱ ምክንያት የሚከሰት የመድሃኒቶች የመጠቀሚያ ጊዜ ማለፍ፤ በየመድሃኒት ቤቶቹ ለማከፋፈል የሚወጣዉ ወጪ፣እንዲሁም ለማከማቻ እና ስራ ማስኬጃ የምናወጣቸዉ ወጪዎች መጨመር የመድሐኒት አከፋፋዬችን ትርፋማነት በእጅጉ እየፈተነው ይገኛል፡፡

በዚሁም ምክንያት የተጣራው ትርፍ ከጠቅላላው ሽያጭ ሲሰላ ከ 3 በመቶ የማይበልጥ ሆኖ ይታያል፡፡

በመሆኑም ይህንን ነባራዊ ሁኔታ በማገናዘብ የ2.5 በመቶ አነስተኛ የግብር ምጣኔው በ መድሐኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አከፋፋዬች ላይ ተግባራዊ መሆኑ ቀርቶ በሂሣብ መዝገብ ወጪና ገቢ ተሰልቶ እንድንከፍል እንዲደረግልን ” ሲል ማህበሩ ጠይቋል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe