የኢትዮጵያ ዲጂታል ሳምንት 2025 ምክንያት በማድረግ ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ አቅራቢው ድርጅት ሁዋዌ በተለያዩ ዘርፎች ያዘጋጀው ጉባኤ “የማሰብ አቅምን ማጉላት ለፋይናንስ ” በሚል መሪ ቃል ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም.የማጠቃለያ መርሃ ግብሩን በስካይላይት ሆቴል ተከናውኗል ።

በማጠቃለያው የሁዋዌ ፋይናንስ ጉባኤ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የሁዋዌ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሃሀሪ ካስተላለፉ በኋላ የፋይናንስ አገልግሎቱን ይበልጥ ለማጠንከርና የተሻለ ደረጃ ለማድረስ ዘመኑ ያፈራቸውን የዲጂታልና የሰውሰራሽ አስተውሎት በሚገባ ጥቅም ላይ ማዋል ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የፋይናንስ ዘርፉ በተለይ ባንኮች ላይ በየጊዜው በሚተዋወቁ የዲጂታልና የሰውሰራሽ አስተውሎት መበልፀግ ምክንያት ስርነቀል የሆነ ለውጥ በማሳየት ላይ እንደሚገኙ በጉባኤው ተገልፆ ደህንነቱን የተጠበቀ ቀልጣፋና ቀላል የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚቻልበት ዕድሉ የሰፋ እንደሆነ ተነግሯል ።
በዲጂታልና የሰውሰራሽ አስተውሎት ታግዞ የሚከናወን የፋይናንስ አገልግሎት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ሁነኛ ሚና እንደሚጫወት በጉባኤው ላይ ጥናታዊ ፅሁፎቻቸውና ምክረ ሃሳባቸውን ያቀረቡ ባለሞያዎች አስገንዝበዋል።
በሁዋዌ የተዘጋጀው የፋይናንስ ጉባኤ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የውይይት መድረክና በቀጣይ መከናወን ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቷል ።

