የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ በውጭ ምንዛሬ እለታዊ ተመን ላይ የ10 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ

ባንኩ 1ሺ ዶላር ለሚዘረዝሩ ደንበኛዎቹ የ10ሺ ብር ጭማሪ እንደሚሰጥ ገልጻል፡፡

በባንኩ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ስሌት ዛሬ አንዱ የአሜሪካን ዶላር በ151.3196 ሳንቲም ከእነጭማሬው እየተዘረዘረ ነው፡፡ ዳሽን ባንክም በዓሉን አስመልክቶ በእያንዳንዱ የውጭ ምንዛሬ መደበኛ ተመን ላይ የአምስት ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ይህ የአምስት ብር ጭማሪ እስከ ጥቅምት 8/2018 እንደሚቆይም ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ

ለኢትዮጽያዊያን ዳያስፖራዎች የ50 ቢሊዮን ብር ብድር ተዘጋጅቷል ተባለ፡፡ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራዎች ብደር ለመስጠት 50 ቢሊዮን ብር አዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡

ባንኩ ይህንን ያስታወቀው በባንኩ ፕሬዝዳንት የተመራው ቡድን በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ከዳያስፖራ ማህበር አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ወቅት ነው፡፡

በዚህም መሠረት ባንኩ ለዳያስፖራው ለኢንቨስትመንት፡ቤት እና መኪና ለመግዛት የሚውል የ50 ቢሊዮን ብር በድር መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe