የኢትዮጽያ ካፒታል ገበያ ከ9 ቀናት በፊት እኔ የማላውቀው ባንክ አለ ካለ በኋላ ለአምስት የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
የመጀመሪያው የኢንቨስትመንት ባንክ ነኝ ብሎ ራሱን የሚያስተዋውቀውን ታኪሎ ኢንቨስትመንት ባንክን እንደማያውቀው ካሳወቀ ወዲህ ነው ለ5 የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ የሰጠው፡፡
ይህ ውሳኔ በኢትዮጽያ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢንቨስትመንት ባንኮችና የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ ፈቃድ የተሰጠበት ነው፡፡
በተጨማሪም አጠቃላይ ፈቃድ የተሰጣቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር ከአራት ወደ ዘጠኝ ከፍ አድርጎታል ተብሏል፡፡
ሲቢኢ አ.ማ-ኢንቨስትመንት ባንክ፡ ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ-ኢንቨስትመንት ባንክ፡ ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ -የሰነድ ሙዓለንዋይ ገበያ አከናዋኝ፡ኤች ኤስ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስ ኃ.የተ.የግ.ማ-የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ፡ኢኩዢን የሰነድ ሙዓለንዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ፈቃድ የተሰጣቸው ድርጅቶች ናቸው ተብሏል፡፡//

