የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው ዝርዝር ውስጥ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ የሚወዳደሩበት ስፍራ አንዱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ አህመድ በጎማ 2 የምርጫ ክልል ላይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓርቲያቸውን ወክለው በእጩነት መቅረባቸውንም ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ታዲያ በዚህ የምርጫ ክልል ላይ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ለህዝብ ተወካች ምክር ቤት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር እንዲፎካከሩ ማቅረባቸውም የምርጫ ቦርድ ዝርዝር ያመለክታል።
በምርጫ ክልሉ ላይ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና እናት ፓርቲ እጩዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ለመወዳደር መቅረባቸው ታቀዋል።
በዚህም መሰረት አቶ ካሊድ ጀማል ሀይደር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)ን ወክለው በእጩነት የቀረቡ ሲሆን፤ አቶ ዳግም ዋሪሶ ካዎ ደግሞ እናት ፓርቲን ወክለው በእጩነት ቀርበዋል።
ሁለቱ የኢዜማ እና የእናት ፓርቲ እጩዎች ከጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ጋር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ የሚፎካከሩ ይሆናል።
[Al ain]