የኢጋድ አባል አገራት የአንድ ቪዛ ስርዓት ዝርጋታ ላይ ምክክር አደረጉ

በኢጋድ አዘጋጅነት መቀመጫቸውን ጂቡቲ ያደረጉ የኢጋድ አባል አገራት አምባሳደሮች ዛሬ ነሐሴ 21/2015 በቀጠናው ነፃ የሰዎች ዝውውር ስምምነት ፕሮቶኮል መውጣቱን ተከትሎ፤ የአንድ ቪዛ ስርዓት ዝርጋታ ላይ ምክክር አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የታደነሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ኢትዮጵያን ይህንን ፕሮቶኮል መፈረሟን በመጥቀስ፤ በቀጠናው የጋራ ኢ-ቪዛ ስርዓት መዘርጋት ቀልጣፋ የአገልገሎት አሰጣጥ እንዲኖር እና የጋራ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲጠነክር የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

የአንድ ቪዛ ጽንሰ-ሀሳብ ዜጎች ለእያንዳንዱ አባል አገራት በርካታ የቪዛ ጥያቄ ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው አንድ የጋራ ቪዛ ብቻ በመያዝ ጎብኚዎች፣ ምሁራን እና የንግድ አካላት በቀላሉ መንቀሳቀስ የሚችሉበት እና በአባል አገራቱ መካከል የባህል፣ የንግድ፣ የቴክኖሎጂ፣ የመሠረተ-ልማት እና የህዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት መሆኑን በውይይቱ በስፋት ተነስቷል።

ይህም አሠራር ከአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063 ጋር የሚጣጣም መሆኑን እና የዚህም ማሳያ እ.ኤ.አ በ2018 የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) አህጉራዊ የገበያ ትስስር ለመፍጠር የአፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ማቋቋሚያ ስምምነትን ማፅደቁ የአፍሪካ ኅብረትን በይበልጥ ማበረታታቱ መገለጹን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በኢጋድ በአንቀፅ 7 እና 13 ላይ የኢጋድ አባል አገር ዜጎች በነፃ የመዘዋወር እና የመኖር መብትን መሠረት በማድረግ እ.ኤ.አ በ2017 ኢጋድ ኤም.ኤስ በነፃ የመንቀሳቀስ ሂደቱን ለማስጀመር የተለያዩ ቴክኒካል ኮሚቴዎችን አቋቁሞ ምክክር ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የነጻ እንቅስቃሴ ስምምነት ፕሮቶኮሉም እ.ኤ.አ በየካቲት 2020 በኢጋድ ኤም.ኤስ የውስጥ ጉዳይ እና ሰራተኛ ሚኒስትሮች መጽደቁ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe