የኤሌክትሪክ ሃይል ስርቆት የፈጸሙ እስከ 1 ሚሊዮን ብር የሚቀጡበት መመሪያ ስራ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡
በተሻሻለው መመሪያ መሰረት የሃይል ስርቆት የፈጸመ መኖሪያ ቤት ወይም ግለሰብ 20ሺ ብር ይቀጣል ተብሏል፡፡
የከፍተኛ ኢንደስትሪዎች ለሚፈጽሙት የሃይል ስርቆት ደግሞ 1 ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጻል፡፡
በበጅት ዓመቱ 11 ወራትም 298 ደንበኞች የሃይል ስርቆት መፈጸማቸውን አገልግሎቱ አሳውቋል፡፡
ይህም ስርቆቱ በገንዘብ ሲሰላ 259 ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንዲደርስብኝ አድርጓል ብሏል፡፡
አገልግሎቱ ፈትኖኛል ያለውን የሃይል ስርቆት ለመቀነስ ተሻሽሏል ባለው መመሪያ የሃይል ስርቆት ፈጽሞ የተገኘ የንግድ ቤት 500ሺ ብር ዝቅተኛ ኢንደስትሪ 750ሺ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል ብሏል፡፡
ከፍተኛ ኢንደስትሪዎች ደግሞ ለሚፈጽሙት የሃይል ስርቆት 1ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደሚጣልባቸው ይፋ አድርጓል፡፡/

