የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተፈጠረው የኃይል መቆራረጥ ችግር ለመጀመሪያ ጊዜ ይቅርታ ጠየቀ!

የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ሳምንታት በልዩነት ለተፈጠረው የኃይል መቆራረጥ ችግር ይቅርታ ጠየቀ፡፡ የአገልግሎቱ ኃላፊ ገበየሁ ረጋሳ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በልዩነት በተለያዩ ምክንያቶች የኃይል መቆራረጥ በመዲናዋ ተከስቷል ብለዋል።

ከምክንያቶቹ መካከል የአየር ንብረት ጋር የተያያዘ ሲሆን በተለይ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የጣለው ከፍተኛ የበልግ ዝናብ የኤክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በመዲናዋ ከሚገኙ 137 መጋቢዎችም በ50ዎቹ ላይ ጉዳት ማድረሱን ገልጸው ብልሽቱን ቶሎ አለማግኘት ችግሩን አባብሶታል ብለዋል።ሌላው በተለይ በመዲናዋ ምዕራብ እና ደቡብ እየተሰሩ የሚገኙ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን እንዲሁም የማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ የሚሰራ የጥገና ስራ ለኃይል መቆራረጡ አስተዋፆ አድርገዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ስርቆቶችም ለችግሩ መፈጠር በምክንያትነት ተነስቷል።ችግሩን ለመፍታትም ለፕሮጀክት የሚቋረጥ የኤክትሪክ አገልግሎት ከማቆም ጀምሮ ኮንስትራክሽን ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን ወደ ጥገና በማዘዋወር ችግሩን ለመፍታት ጥረት መደረጉን ገልፀው በዘላቂነት ለመፍታት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል።

[Walta]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe