የኤሌክትሪክ ዋጋ  ጭማሪ  መደረጉን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ

የካርድ የቅድመ ክፍያንና የመብራት ቆጣሪን በተመለከተ የአሰራር ክፍተት መኖሩን እና ያለአግባብ በእጥፍ እየከፈሉ በመሆናቸው መቸገራቸውን ነዋሪዎች  ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
ለኢንቨስትመንት ስራ፤ የውስጥ አሰራርን ለማቀላጠፍ፤ መቆራረጥን ለማስቀረት እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ከውጪ የሚገቡ በመሆናቸው ያንን ለማስተካከል እና አሰራሩን ለማዘመን ጭማሪ ተደርጓል፡፡ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግኝኑነት ሀላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ናቸው፡፡
በአንድ ጊዜ ስለማይቻል ከ2011 ጀምሮ በአራት ዙር የኤሌክትሪክ የአገልግሎት ክፍያ ላይ የዋጋ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን 2014 ላይ እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት አቶ በቀለ የሶስተኛው ዙር ጭማሪ ጥር ላይ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ባለመገንዘብ ና ባለማስታወስ ማህበረሰቡ የዋጋ ጭማሪ ተደረገብን በሚል ቅሬታዎችን ሊያነሳ እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡
ከ50 እስከ መቶ ዋት የ40 ሳንቲም ጭማሪ የተደረገ ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ እንደሚጠቀመው የኤሌክትሪክ ፍጆታ መጠን ክፍያው እንደሚጨምርም ተናግረዋል፡፡
ከቆጣሪ ንባብ እና ከቅድመ ክፍያ የካርድ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ ቅሬታ ካለው ያለ አግባብ ወይም በእጥፍ እንድንከፍል ተደርገናል የሚሉ ጥያቄዎች ካሉና በተቋሙ ችግር ከሆነ የእፎይታ ግዜ በመስጠት ማስተካከያ የሚደረግባት መሆኑንን ተናግረዋል፡፡
ከኤሌክትሪክ ክፍያ ጋር በተያያዘ ለሚነሱ ቅሬታዎች ማህበረሰቡ በአቅራቢያው ባለው አገልግሎት መስጫ ተቋም ሪፖርት በማድረግ ተገቢውን ምላሽ ማግኘት እንደሚችሉም ገልጸዋል፡፡/አሐዱ ራዲዮ 94.3/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe