“የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማምቷል” ጠ/ሚ ዐቢይ

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በኢኮኖሚ ትብብር አብረው መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡

የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሕወሓት ወደ አስመራ ሮኬት በመተኮሱ መሆኑን ጠ/ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባወጡት መግለጫ ፣ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በአስመራ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የኤርትራ መንግሥት ጦሩን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት መስማማቱን ገልጸዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት ወዲያውኑ ተክቶ የድንበር አካባቢዎችን ይጠብቃል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የመግባቱ ምክንያት ሕወሓት ወደ አስመራ ሮኬት መተኮሱ መሆኑን የጠቀሱት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ፣ ይህ የሕወሓት ድርጊት “የኤርትራን መንግሥት የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጦ በመግባት ከተጨማሪ ጥቃቶች ራሱን እንዲከላከል እና ብሔራዊ ደኅንነቱን እንዲጠብቅ አነሣሥቶታል” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው እና በኢኮኖሚ ትብብር ፍላጎታቸው ላይ አብረው መሥራታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አመለክተዋል፡፡ በ2010 ዓ.ም. በተጀመረው መሠረት በሁለቱ ሀገራት መካከል በመተማመን መንፈስ “መልካም የጉርብትና ግንኙነታችንን መገንባታችንን እንቀጥላለን” ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ “በተለይም፣ በትግራይ ክልል እና ከድንበር ማዶ ባሉ ኤርትራውያን ወገኖቻችን መካከል በመተማመን ላየ የተመሠረተ ግንኙነትን መመለስ በእጅጉ ያስፈልጋል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት ከሰዓት ላይ ነበር አስመራ የገቡት፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe