የኤርትራ ባለሥልጣናት ወደ ሱዳን አቅንተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ጋር መወያየታቸው ተገለጸ

ባለስልጣናቱ ከፕሬዘዳንት ኢሳያስ የተላከውን መልእክስት ለአብደላ ሀምዶክ አስረክበዋል፡፡

የኤርትራና እና የሱዳን ባለስልጣናት በኢትዮጵያ አሁናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ተብሏል፡፡

የኤርትራና እና የሱዳን ባለስልጣናት በኢትዮጵያ አሁናዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል ተብሏል፡፡

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረአብ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር መወያየታቸውን ሱዳን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ሁለቱ የኤርትራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር በሁለትዮሽ ግንኑነት ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን ነው የሱዳን ዜና አገልግሎት የዘገበው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሁለቱ ሀገራት ባለስጣናት በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡

የሱዳን ዜና አገልግሎት የአስመራ እና የካርቱም ባለስልጣኖች በኢትዮጵያ አሁናዊ ጉዳዮች ውይይት ማድረጋቸውን እንጅ ዝርዝር ጉዳዮች ምን እንደነበሩ አልገለጸም፡፡

ኡስማን ሳሌህ እና የማነ ገብረአብ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተላከ የቃል መልዕክትን ለአብደላ ሃምዶክ ማድረሳቸውም ተገልጿል፡፡ በባለስልጣኖቹ ወደ ካርቱም የተላከው መልዕክትም በካርቱም እና አስመራ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe