የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ!

የእስራኤል ካቢኔ በሐማስ ታግተው የሚገኙ 50 ሰዎችን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አጸደቀ።የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት 50 ታጋቾች በአራት ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ አስታውቋል።

በምላሹ እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምታለች።በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ከሚለቀቁ 50 ታጋቾች በተጨማሪ “10 ታጋቾች በተለቀቁ ቁጥር አንድ ተጨማሪ የተኩስ አቁም ቀን ይኖራል” ተብሏል።

ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ230 ያላነሱ ሰዎችን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።ሐማስ እና እስራኤል በደረሱት ስምምነት መሠረት በቅድሚያ ታግተው የሚገኙ ሴቶች እና ሕጻናት ነጻ ይወጣሉ ተብሏል።

[BBC]

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe