የእስራኤል ጦር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሀይል ትጠቀማለች ሲል በኢራን ላይ ዛተ

የእስራኤል ጦር ቴህራንን አስጠነቀቀ። ጦሩ እስራኤል ሀይል መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ባገኘችው ጊዜ ትጠቀማለች ሲል በኢራን ላይ ዝቷል።
ሁለቱም ባላንጣ ሀገራት ዳግም ወደ ጦርነት እንዳያመሩ ተሰግቷል። ለእስራኤል ስጋት የሆኑ ምልክቶች በየትኛውም ቦታ በኢራን ውስጥ ቢሆንም ከተመለከትን ከማጥቃት ወደኋላ አንልም ሲሉ የጦሩ አዛዡ ኢያር ዛሚር ገልጸዋል።
የጦሩ ዋና አዛዥ ኢያር ዛሚር ጦራችን በቅርብም በሩቅም ያሉ ጠላቶቻችን ለማጥቃት የሚያግደው የለም ብለዋል። ጦር አዛዡ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ ካለው ከረጅሙና ከውስብስቡ ጦርነት ጀርባ ኢራን አለች ብለዋል።
በእስራኤል ዙሪያ ያሉ ተዋጊዎችን የምታደራጀው ኢራን መሆኗ ይታወቃል በማለትም አንስተዋል። ኢራን ከሰኔው ጦርነት በኋላ የባላስቲክ ሚሳኤሎችን በገፍ እያመረተች እንደሆነ በሚወጡ ዘገባዎች እየታየ ነው።
እስራኤል የኢራንን የኒውክሌር ፕሮግራም በህልውና ላይ የተጋረጠ ስጋት አድርጋ ነው የምትመለከተው።
ኢራን በዚህ ስዓት ሌላ ዙር ጦርነት የሚመጣ ከሆነ እርሱን ለመመከት በዝግጅት ላይ መሆኗን እየገለጸች ነው። በተጨማሪም ባለፈው የ12 ቀናት ጦርነት ወቅት የወደሙብኝን በሙሉ ዳግም እየገነባሁ ነው እያለች ነው።
አሁንም እንደከዚህ ቀደሙ ያልተሳካ ሙከራ በእኛ ላይ የሚያደርጉ ከሆነ ምንም ማሳካት እንደማይችሉ ይወቁት በማለት ገልጻለች። ኢራን ውጤት አልባው ሙከራ የምትለው የ12ቱን ቀን ጦርነት ነው።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግች እውነታው በጦርነቱ መሠረተ ልማቶቻችን ተጎድተውብናል፤የቴክኖሎጂ አቅማችን ግን በቦምብ ፍንዳታ የሚጠፋ አይደለም ብለዋል። ለሰላማዊ አገልገሎት የኒውክሌር ፕሮግራማችንን ከመጠቀም የሚገታን ሀይል አይኖርም በማለት ገልጸዋል። አክለውም መቼም ቢሆን ከሰላማዊ አገልግሎት ውጪ አናውለም ይህን ማረጋገጥ እችላለሁ ብለዋል።
እስራኤል በሰኔ ወር በኢራን የኒውክሌር እና የሚሳኤል መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት በመክፈቷ ነበር ጦርነቱ የተጀመረው።
በዚያው የጦርነት ጊዜም በኢራን የጦር አቅም ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ነበር የደረሰው። 1000ሺ የሚሆኑ ሰዎች ኢራን እንደተገደለባት መግለጿም ይታወሳል።
በወቅቱም ከ500 በላይ የባላስቲክ ሚሳኤል እና ከ1000 በላይ ደሮኖችን በእስራኤል ላይ ተጠቅማ 32 ሰዎች ተገድለው 3ሺ የሚጠጉት ደግሞ በእስራኤል መቁሰላቸውን የታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘገባ አስታውሷል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe