የእስራኤል ጦር ከኢራን ጋር አዲስ ውጊያ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተሰማ

ካን የተሰኘው የሀገሪቱ የዜና ምንጭ በስም ያልጠቀሳቸው የደህንነት ምንጮቹን ገልጾ ባሰራጨው ዘገባ አሜሪካ በኢራን ላይ በምትወስደው ርምጃ እስራኤልም ትቀላቀላለች ብሏል፡፡

ይህ ሪፖርት ይፋ የሆነው ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ እና ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ30 ደቂቃ ያህል በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ ነው፡፡

ዘገባው አክሎም የመሪዎቹ ንግግር የተደረገው አዲስ ጦርነት ከኢራን ጋር ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት በዚህ ስዓት ነው ብሏል፡፡

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በቻይና በነበራቸው ጉብኝት ወቅት ዳግም ግጭቶችን ከመቀስቀስ ይልቅ ነገሮች በዲፕሎማሲ እንዲፈቱ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ከቤጂንግ በኩል ተነግሯቸዋል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት ቴህራን በዚህ ስዓት ትኩረቷ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሳይሆን ጦርነቱ እንዲቆም በሚለው ላይ ነው ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም ቴህራን እና ዩናይትድስቴትስ ኢራን ባቀረበችው የሰላም አማራጭ ዙሪያ ንግግሮች ለውጥ እንዲያመጡ አስተያየቶችን እየተለዋወጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe