የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት “የአማራ ብሄር ጽንፈኞች” ሲል የገለጣቸውን ኃይሎች እደመስሳለሁ ማለቱ ተሰማ

አብን በበኩሉ  የአማራ ክልል ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል የመሬት ወረራ ፈፅመዋል ማለቱን አውግዟል፤

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት “የአማራ ብሄር ጽንፈኞች” ሲል የገለጣቸውን ኃይሎች እደመስሳለሁ ሲል በኮምንኬሽን ቢሮው በኩል መዛቱን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

የቢሮው ሃላፊ ኃይሉ አዱኛ በኦሮምኛ ቋንቋ በስጡት መግለጫ፣ ጽንፈኛ ያሏቸው የአማራ ክልል ኃይሎች በምሥራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ እና በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ነዋሪዎችን አፈናቅለዋል፤ ንብረትም ዘርፈዋል በማለት ከሰዋል።

ሃላፊው አያይዘውም፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በቅርቡ የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የጋራ ኮሚቴ እንዳቋቋሙ ተናግረዋል። ጽንፈኛ ያሏቸው የአማራ ኃይሎች በትክክል የትኞቹ እንደሆኑ ግን ሃላፊው አላብራሩም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦፌኮ የአማራ ክልል ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ምሥራቅ ሸዋ ዞኖች የመሬት ወረራ እያካሄዱ ነው በማለት መክሰሱን አብን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አውግዟል።

ኦፌኮ የጠቀሳቸው አብዛኞቹ አካባቢዎች የአማራ ብሄር ተወላጆች በማንነታቸው ተለይተው በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚጨፈጨፉባቸው እንደሆኑ አብን ገልጧል። ኦፌኮ ይህን አደገኛ መግለጫ ያወጣው፣ በኦሮሞ ፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን የፖለቲካ ሽኩቻ እና ከኦነግ ሸኔ ጋር የሚደረገውን ግጭት ለማርገብ ሲል ነው ሲል ከሷል። በአገሪቱ ያሉ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ተቀራርቦ በመስራት ብቻ እንደሆነ ፓርቲው ጨምሮ ገልጧል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe