የከተማ አስተዳደሩ ሰሞኑን በወጣው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር መከሰቱን አመነ

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሐምሌ 01 ቀን 2014 በወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ የዳታ ማጭበርበር ድርጊት በመከሰቱ ሁኔታውን እያጣራ እንደሚገኝ እና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ከዕጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት በኋላ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ ሲጀመር በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነት ተገኝቶበታል፡፡
በእስካሁኑ የማጠራት ስራም ላልቆጠቡ ሰዎች እጣ መውጣትን ጨምሮ የተለያዩ የተዓማኒነት ጉድለቶች ታይተዋል ነው ያለው፡፡
በጉዳዩ የተጠረጠሩ ባለሙያዎች እና አመራር በቁጥጥር ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ከዚህ በመነሳትም “የቤት ማስተላለፉን ሂደት ግልፅነት ለማስፈን ሲባል እና ውጤቱን የሚያዛባ ተግባር ሲያጋጥም መልሰን ኦዲት እንዲደረግ በገባነው ቃል መሰረት የተፈጠረውን ችግር ከጉዳዩ ገለልተኛ በሆኑ በሚመለከታቸው ተቋማት የማጣራት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል” ብሏል፡፡
ሒደቱን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ለቤት ተመዝጋቢዎችና ለመላው የከተማዋ ነዋሪ እንደሚያሳውቅ የገለጸው አስተዳደሩ÷ተመዝጋቢዎች እንደተለመደው በከፍተኛ ትዕግስት እንዲጠባበቁም ጠይቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe