የካሜሩን እና የአይቮሪኮስት ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች አዲስ አበባ ላይ ተያዙ፤

የካሜሩን እና የአይቮሪኮስት ዜግነት ያላቸው ሁለት ግለሰቦች አዲስ አበባ ላይ ተያዙ፤

ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን  ሲያባዙ ነው የያዝኳቸው ብሏል ፖሊስ

ግለሰቦቹ የካሜሩን እና የአይቮሪኮስት ዜግነት ነው ያላቸው ፣ ህገ-ወጥ የገንዘብ እጥበትና ብዜት ወንጀል ላይ የተሰማሩ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ ብርቱ ክትትል በማድረግ  በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል -በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ኤድናሞል አካባቢ በሚገኘው ሞዛይክ ሆቴል ውስጥ፤

ሁለቱ ግለሰቦች አንድ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማጠብና ለማባዛት ከአንድ ሰው ጋር ተስማምተው ናሙናውን በማሳየት ላይ እያሉ  ነው በሆቴል ውስጥ እጅ ከፍንጅ የተያዙት፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረጉት ፍተሻ ሁለት ጥቁር ቀለም የተቀባ ሁለት ባለ 100 እና አንድ ባለ 20 የአሜሪካ ዶላር፣ 3 ሺህ የታንዛኒያ ገንዘብ፣ አንድ ባለ 10 የተባበሩት አረብ ኢምሬት ድርሀም፣ 600 የኬኒያ ሽልንግ፣ 500 የሱዳን ፓውንድ፣ 20 ሺህ የፈረንሳይ ፍራንክ እንዲሁም ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙባቸው የጠቆረ ዶላር መሳይ ወረቀት፣ በተለያዩ ብልቃጦች የተዘጋጀ ፈሳሽና ዱቄት ኬሚካል መሳይ፣ ማስመሪያ እና በርካታ ካኪ ፖስታዎችን በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe