የኮሎምቢያ የብስክሌት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት በቅርቡ ለውድድር ሲቀርቡ ለብሰውት የታዩት ትጥቅ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ የስፖርተኞቹን ልብስ የተመለከቱ ሰዎች ሴቶቹ ራቁታቸውን ወደአደባባይ መውጣታውን ሲቃወሙ ታይተዋል፡፡ ሲጣራ ግን ነገሩ ወዲህ ነው ይላል ሮይተርስ የስፖርተኞቹን ፎቶግራፍ አስደግፎ ባወጣው ዘገባ፡፡
ስፖርተኞቹ በምስል ሲታዩ ራቁታቸውን ይምሰሉ እንጂ ከሰውነት ቀለማቸው ጋር ሆን ተብሎ ተመሳስሎ በዲዛይን የተሰራ ልብስ አድርገዋል፡፡ በተለይም በፊልምና በፎቶ የሚመለከታቸው ሰው ስፖርተኞቹ ራቁታቸውን የመጡ ሊመስለው ይችላል ብሏል፡፡

