የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች የሥራ ማቆም አድማ መቱ

በ2011 ዓም በዞኑ ምክር ቤት የተጠየቀው በክልል የመደራጀት ጥያቄ ገቢራዊ ይሁን የሚለው ለአድማው መነሾ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ የሥራ ማቆም እና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማው ዛሬ ከማለዳው አንስቶ የተካሄደው ትናንት ሐሙስ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የአድማ ጥሪ መተላለፉን ተከትሎ ነው፡፡
በአድማው በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ጎማ ያቃጥሉ የነበሩ ወጣቶች ከፀጥታ አባላት ጋር ከፈጠሩት መጠነኛ ጭቅጭቅ በስተቀር ሂደቱ ሰላማዊ እንደነበር የከተማይቱ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ DW በስልክ ገልጸዋል፡፡ በከተማው ከኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በስተቀር ሁሉም የመንግሥትና የንግድ ድርጅቶች ዝግ ሆነው መዋላቸውን ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡
የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ነሀሴ 5 ቀን 2014 ዓም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ጉራጌ አምስት ዞኖችና እንድ ልዩ ወረዳን በማካተት የሚመሠረተው አዲስ ክልላዊ መንግሥት አካል እንዲሆን የቀረበለትን ጥያቄ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ወሳኔውን ተከትሎ የዞኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ በርካታ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሲነሱ ከፊሎቹ ለእሥር መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው ፡፡ ዛሬ በዞኑ ዋና ከተማ ወልቂጤ የተካሄደው የሥራ ማቆም እና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ የ2015 ዓም ከገባ ወዲህ ለሦስተኛ ጊዜ የተጠራ ነው፡፡
SourceDW 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe