የወተት ዋጋው እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ መጨመሩ ወላጆችን አስጨንቋል

በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች ለህጻናት ወሣኝ የሆኑ የወተት ምርቶች በተለይ ‘ ሁለት ቁጥር ‘ ማግኘት እንዳልቻሉ ወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

” ይኸው የወተት ምርት ከሳምንታት በፊት በ950 ብር ሲሸጥ ነበር የምንዛሬ ዋጋ ከጨመረ ወዲህ ግን እስከ 1800 ብር ገብቷል ” ብለዋል።

” ያውም ይሄ ዋጋ ወተቱን ማግኘት ስንችል ነው ” ሲሉ አክለዋል።

አንድ ቁጥርም በገበያ ላይ እጥረት እንዳለ ከወላጆች ሰምተናል። ይበልጥ ግን ቁጥር ሁለቱን ማግኘት ፈተና እንደሆነና ዋጋም ለወላጅ የሚቀመስ እንዳልሆነ ለመረዳት ችለናል።

ያነጋገርናቸው የፋርማሲ ባለሙያዎችና ወላጆች የወተት ምርቶቹ ሀገር ውስጥ ጠፍተዋል ብለው እንደማያምኑ የተያዘ ክምችት ሊኖር ይችላል ብለው እንደሚገምቱ ለዚህም የሚመለከታው አካል ኃላፊነቱን በመወጣት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የወተት ዋጋው እጅግ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ መጨመሩ ወላጆችን አስጨንቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe