የውጭ ሀገር ዜጎች ቤት እንዲኖራው የሚፈቀቅደው ረቂቅ የኢንቨስትመት ሕግ አነጋጋሪ ሆኗል

በኢትዮጵያ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ከታወጀበትና መተግበር ከጀመረበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ አሁን ስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር 769/2004 ጨምሮ በ1984፤በ1988፤እና በ2004 ዓ.ም መሠረታዊ ዓላማቸው ኢንቨስትመትን መሳብ ማበረታታትና ማስተዳደር ላይ ያተኮሩ አዋጆችና ደንቦች ፀድቀዋል፡፡
ስራ ላይ ያለው የኢንቨስትመንት ህግ ለመንግስትና ለኢትዮጵያውያን ብቻ የከለላቸው የስራ መስኮችን መነሻ በማድረግ ባለሀብቶችን በሶስት ከፍሎ ነው ያስቀመጣቸው፡፡ በዚህም መሠረት የሀገር ውስጥ ባለሀብት፤ የውጭ ሀገር ባለሀብትና ኢትዮጵያዊ ባለሀብት በማለት በሶስት ነው የከፈላቸው፡፡አሁን ለፖርላማው የቀረበው ረቂቅ የኢንቨስትመንት አዋጅ ግን በሁለት ከፍሎ ነው ያቀረባቸው፡ ፡
የመጀመሪያው የሀገር ውስጥ ባለሀብት በማለት በዚህ ክፍል ውስጥ መንግስትን ፤ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ እንደ ኢትዮጵያውያን እንዲቆጠሩ ህጉ የሚፈቅድላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያንና በዓለም አቀፍ ስምምነት ተመሳሳይ መብት የሚያገኙ የውጭ ሀገር ዜጎችን የሚይዝ ሲሆን
ሁለተኛው መደብ የውጭ ሀገር ዜጎችን ብቻ የሚመለከት ይሆናል ተብሏል፤ በመሆኑም የውጭ ሀገር ዜጋ ተብለው በውጭ ሀገር ፖስፖርት የሚንቀሳቀሱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አሁን እንደ ኢትዮጵያዊ ነው የሚስተናገዱት ማለት ነው፤ ይሄ ብቻ አይደለም፤ ቋሚ መኖሪያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጭ ሀገር ዜጎችም ምንም እንኳ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ባይሆኑም እንደ ኢትዮጵያዊ ይታያሉ ተብሎ ተደንግጓል፡፡
ይህም ማለት እነዚህ ቋሚ መኖሪያውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጭ ሀገር ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ እዚህ ሀገር ይዘዋቸው የመጡት ቤተሰቦቻቸውም እንደ ኢትዮጵያዊ ይቆጠራሉ ሲል ህጉ ይደነግጋል፤
ለእነዚህ የውጭ ሀገር ባለሀብቶች ሌላም ከዚህ በፊት ያልነበረ መብት ይፈቅድላቸዋል ረቂቅ የኢንቨስትመት ህጉ፤ እነዚህ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖሩ ከፍ ያለ ኢንቨስትመንት ስላላቸው ከዚህ በፊት የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲያፈሩ አይፈቀድም ነበር፤ አሁን ግን የፈለጉትን ያህል መኖሪያ ቤት ሊገዙ ይችላሉ፤
በቪዛ በኩልም ለውጭ ሀገር ባለሀብቶች የተሻሻለ ድንጋጌ ተቀምጦላቸዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ የውጭ ሀገር ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ለመሰማራ ወይም ኢንቨስትመንታቸውን ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ ለማቅለል በሚል ከሶስተኛ ሀገር ሆነው የቪዛ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ፤ ይህ ቪዛ ለባለሀብቱ ብቻ ሳይሆን በድርጅቱ ውስጥ ባለድርሻ ለሆኑ ሰዎች በሙሉ አምስት ዓመት የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ ይሰጣቸዋል ይላል ህጉ፡፡
ከባለቤቶቹ ውጭ ለድርጅቱ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ደግሞ የሶስት ዓመት የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ ያገኛሉ፡፡
ከጥቂት ዓመታት በኋላ የመኖሪያ ቤት ዋጋ አሁን ካለበት በሶስትና በአራት እጥፍ ሊመነደግ ይችላል ፤ምክንያቱ ደግሞ የኢንቨስትን ህጉ ለውጭ ሀገር ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲገዘዙ ስለሚፈቅድ ቤት ሻጮች ግብይታቸውን በዶላር በማድረግ ሀገሪቱ አብዛኛዎቹ የማይንቀሳቅስ ንብረት ባለቤቶች የውጭ ሀገር ዜጎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ከወዲሁ ተፈጥሯል፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe