የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተከትሎ፣ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችና ላኪዎች በእጃቸው ያለውን ምርት በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ የቡና ዋጋ እየቀነሰ ነው
የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ተከትሎ፣ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎችና ላኪዎች በእጃቸው ያለውን ምርት ለከፍተኛ ኪሳራ ሳይዳረጉ በፍጥነት ለገበያ እንዲያቀርቡ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላለፈ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት፣ ባለፉት ሁለት ወራት የዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ ከነበረበት 4 ዶላር ወደ 2 ነጥብ 8 ዶላር ዝቅ ማለቱንና በቀጣይም እስከ 2 ነጥብ 5 ዶላር ሊወርድ እንደሚችል በመተንበዩ፣ አቅራቢዎች ምርቱን በእጃቸው አቆይተው ለከፍተኛ ኪሳራ እንዳይዳረጉ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ በፍጥነት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብና ወደ ውጭ መላክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በበጀት ዓመቱ ከተመረተው 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ቡና ውስጥ 600 ሽህ ቶኑን ወደ ውጭ በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ ይህንን ስኬታማ ለማድረግም አቅራቢዎች ከኮሜርሻል ቡና ይልቅ የተሻለ ዋጋ በሚያስገኘው የስፔሻሊቲ ቡና ጥራት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ መጠየቁን ኢፕድ ዘግቧል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም ቡናን ከአንድ ዓመት በላይ አሳድሮ ማቆየት፣ በኮንትሮባንድ ወይም በህገ-ወጥ መንገድ ለመሸጥ መሞከር በህግ የሚያስቀጣና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ የሚጎዳ ተግባር መሆኑን ዳይሬክተሩ አስገንዝበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe