የዓለም የህዝብ ቁጥር በ2037 አስር ቢሊዮን ይደርሳል ተባለ

የዓለም የህዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን ሆነ!የተባበሩት መንግስታት ባወጣው የህዝብ ቁጥር ትንበያ መሰረት የዓለም የህዝብ ቁጥር ስምንት ቢሊዮን ደፍኗል።

የሞት ምጣኔ ሲቀንስ ሰዎች በምድር ላይ የሚኖሩበት እድሜ ምጣኔ ጨምሯል።እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2019 አማካኝ ሰዎች በህይወት የመኖር ምጣኔ 72.8 አመት ሲሆን ይህም በ2050 ላይ ወደ 77.2 አመት ከፍ ይላል ተብሏል።

የዓለም የህዝብ ቁጥር በ2037 አስር ቢሊዮን እንደሚደርስም የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል።በ2020 የዓለም የህዝብ ቁጥር እድገት አንድ በመቶ የቀነሰ ሲሆን ይህም ከ1950 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በአሁኑ ወቅት የዓለም አማካኝ የወሊድ ምጣኔ 2.3 በመቶ መሆኑ ታውቋል።በዜጎች መካክል ያለው የገቢ መጠን እየሰፋ መምጣት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ድህነት እና ጦርነት አሁንም የዓለም ህዝብን እየፈተኑ ያሉ ችግሮች ናቸው ብሏል የተባበሩት መንግስታት።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe