የዓመቱ ምርጦች አስቴር በዳኔ/ደራሲና ዳይሬክተር/

በማንነቷ የማታፍር፤ በኢትዮጵያዊነቷ የማትደራደር፤ ሰዎች ምን ይሉኛል ብላ ሀሳቧን ከመግለጽ የማትፈራ አርቲስት ናት አስቴር በዳኔ፤ አስቴር ወደ ኪነጥበብ ቤተሰቦች ጋር  በይበልጥ የተዋወቀችውና በየሰው ቤት የገባችው ‹ጎጆ መውጫ› በተሰኘው የቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማ ይሁን እንጂ ባለፉት 20 ዓመታት ራሷን ሆና ለመውጣት  እርምጃዋን በጥንቃቄ ስታደርግ ነበር፤ ከ ለ ው ጡ በፊትና በኋላ በማህበራዊ ትስሰር ገፆች  ላይ ሀሳቧን በይፋ በመፃፍ እንዲሁም በተጋበዘችባቸው ሚዲያዎች ላይ በድፍረት በመናገር የምትታወቀው አስቴር በተለይም የቀድሞውን ኢህአዴግ መራሹ የህወሃት ቡድን የህወሃትን 40ኛ ዓመት ለማክበር በተጠራው የጉዞ ፕሮግራም ላይ ተገኝታ የደርግ ወታደሮችን ‹ጠላት› እያሉ አሁንም የመጥራታቸው አመንክዮ ፈፅሞ ስላልተዋጠላት ለወቅቱ የሀገር አስተዳዳሪዎችና የስርዓቱ ቁንጮ ባላስልጣናት ፊት ለፊት ነበር ጥያቄ ያቀረበችላቸው፤‹ለምን?›በማለት፡፡

<የዓመቱ ምርጦች ‹ኣርባዕቱ› እንስት ተሟጋቾች>

አስቴር በወቅቱ ለዚህ ጥያቄዋ ዋጋ እንደምትከፍል በብዙ ሰዎች ግምት የነበረ ሲሆን ጉዞው እስከሚጠናቀቅ አብረዋት የነበሩ የሙያ ጓደኞቿ ሳይቀሩ ከእርሷ ጋር መታየት በመተዋቸው ‹ማግለልና መድልዎ› እንደተፈፀመባት በወቅቱ ለቁም ነገር መጽሔት ተናግራ ነበር፤ አስቴር በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ማስተር ማይዶች በራሳቸው ሜዳ ላይ ነጥብ ያስጣለቻቸው አጉል ዝና ፈለጋ ወይል በግብዝነት አልነበረም፤ ግንቦት 20 በየዓመቱ በመጣ ቁጠር የአንድ እናት ልጆች ደም የተቃቡበትን ጦርነት ‹ደመሰስናቸው› እያሉ በጀብደኝነት ማውራታቸው ስላልተዋጠላት ነው ጥያቄውን ያነሳችው፤ የፈለግነውን ብንል የተደመሰሱት ኢትዮጵያውያን የእኛው ልጆች ናቸውና የሚያኮራ ነገር የለውም ማለቷ ነው፡፡ አስቴር ከለውጡም በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንግስት በግልጽ በመደገፍ ሀገሪቱ ለዲሞክራሲዊ ሽግግር የምታደርገውን ሂደት በአውንታዊ መልኩ ስትመለከተው ቆይታለች፤ ያም ሆኖ አጋጣሚውን የተጠቀሙና ‹ትግሉ በእኛ ነው› በሚሉ ብሔርተኞች የታሰበው የዲሞክራሲ ጉዞና መረጋጋት ሲደናቀፍ ‹ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ› የሚለውን ብሂል አልተከተለችም፤ ይልቁንም ለውጡን ለማደናቀፍ በየጊዜው የሚደረጉ አፍራሽ አስተሳሰቦችንና ድርጊቶችን ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ተዋግታለች፤

ሀገር ለማፍረስ  ተብለው  የሚጠቀሱ የፖለቲካ መሪዎችን ንግግሮች ከአፍ ወለምታ በላይ መሆኑን አሳይታለች፡፡በቅርቡም የኦሮሚያው ክልል ፕሬዚዳንት ያደረጉትንና ሾልኮ የወጣውን ንግግር በፈጣሪ ፈቃድ የወጣ መጋለጥ እንደሆነ ከየኛ ቲዩብ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ እንደምታምን ተናግራለች፤ ይህን ንግግር አንዳንዶች የግለሰብ ንግግር ብቻ  አድርገው ሊያቃልሉት ሲሞክሩም ሀሳቡ የቀነጨረ መሆኑን   ከመግልፅ በተጨማሪ ‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ሀሳብ ጀርባ ላለመኖራቸው ወጥተው በአደባባይ እስካልነገሩን ድረስ የእሳቸው ሀሳብም አለመሆኑን እንዴት እናምናለን?› በማለት በይፋ አቋሟን ተናግራለች፤

<የዓመቱ ምርጦች – ኤልሳቤት ከበደ/የሕግ ባለሙያ/>

አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በዚህና በመሰል መድረኮች ላይ ለሃሳቧ ለእምነቷ ሟች መሆኗን መሠረት በማድረግ እንዲህ ብሏታል፤‹በዘመኗ ያለነፃነቷ ኖራ የማታወቅ ልዕልት!አስቴር በዳኔ ትናንት ደደቢት ምሽግ በር ላይ፤ዛሬ ደግሞ አራት ኪሎ ቤተመንግስት ደጃፍ ላይ ዕውነቱን የምትናገር ብቻ ሳይሆን ዕውነቷን የምትኖር የተፈተነች ፅኑ ናት.. ኢትዮጵያዊት ናት!!ኢትዮጵያዊነት ሰብዐዊነት፣የጋራ እኩልነት፣ፍትህ፣ መስዋዕትነት፣ብልፅግናና ደስታ ነው።እነዚህን መገለጫዎቹን ሙሉ በሙሉ አሟልቶ ለሁሉም ዜጋ እኩል የምትነጋና የምትመሽ አገር ትሆን ዘንድ ልሒቃን በተልዕኳዊነት መንፈስ ሊያገለግሏት የምትገባ አገር ናት።አስቴር በዳኔ በአርያነቷ ብዙ ሺ ወጣቶች እንድታፈራ በመረጠችው አካሔድ በመንግስትም በግለሰቦችም ታግዛ ህልሟን ከግብ የምታደርስበት አቅም ሊገነባላት ይገባል።ልቦናዋን፣ህሊናዋንና መንፈሷን ሙስናና ቡድናዊነት ሊያመክነቱ የማትፈቅድ ጠንካራ መሆኑን በተግባሯ አስመስክራለች።› አስቴር ለእውነት መናገር አልያም ከግፉአን ጋር መቆም ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል ታውቃለች፤ ሰሞኑን በሰነዘረችው ሀሳቧ የተነሳም አንዳንድ የብሄርተኛ አክራሪዎች የግል ስልክ ቁጥሯን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ከአቋሟ እንድትንሻራተትና ቃሏን እንድትለውጥ ማስፈራራታቸው አልቀረም፤ የአስቴር ምልሽስ? ‹ይድረስ ለወዳጆቼ…› እንዲሁም ለጠላቶቼ› የሚል ነበር፤ ‹እኔን ዝም ማስባል አይደለም መግደልም ትችላላችሁ። አንዲት ሴት፣ እናት፣ ለሀገሯ የምታስብ፣ ለእናንተ ልጆች የነገ ሀገር ሳይቀር የምትቆረቆር፤ ብቸኛ፣ ጦር መሳሪያም ሆነ ቡድን፤ ተከላካይም ሆነ ጋርድ የሌላት፤ ከፈጠራት አምላክ ውጪ የምትመካበት ነገር የሌላትን ሴት ከተራ እስከ ላይይይ  ጫፍ ድረስ ስታስፈራሩ ይገርመኛል እንጂ አልሸበርም። በዚሁ ለሴት ልጅ ያላችሁን አክብሮት ተረድቻለሁ። ብቻዬን ሆኜንኳ ምን ያህል እንደፈራችሁኝና እንደተሸበራችሁ ለማወቅ በመቻሌ ግን ደስ ብሎኛል። “እውነትና ኢትዮጵያዊነት ውስጥ ኃይልና የእግዚአብሔር ሞገስ አለ!” እናንተም አውልቃችሁ የጣላችሁትን ኢትዮጵያዊነት በማንኛውም ሰዓት እንደነቃችሁ ብትለብሱት ሞገስና ሰላም ይሆናችኃል።›

አስቴር በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ ከምታሰፍራቸው ሀሳቦቿ በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዋልታ ቴሌቪዥን ላይ ‹ጣፋጭ ወግ › የተሰኘ ሀሳብ ላይ ያተኮረ ቃለ ምልልስ ፕሮግራም አዘጋጅታ ማቅረብ ጀምራለች፤ አስቴር በፕሮግራሙ ላይ ራሷን እንድ ጋዜጠኛ ሳይሆን ሀሳብ እንዳላት አንድ ሰው በመቁጠር ከእንግዶቿ ለየት ያለ የህይወት አተያይን ታውጣጣለች፤ ‹ ጋዜጠኛ መሆን አልፈልግም። ሃሳብ አለኝ፤ ሃሳበኞችን እጋብዛለሁ።ፕሮግራሙ ግለሰቦች ላይ ፣ ተቋማት ላይ አያተኩርም፤ ሃሳብ ላይ እንጂ።ማንኛውም ነገር የሚጀምረው ከሃሳብ ነው።ያልተገራ፣ ያልተፈተሸ፣ ያልተብላላ፣ በእውቀት ላይ ያልተመሰረተ ሃሳብ ሁሉ ሀገር ያፈርሳል።› ትላለች፡፡ ‹ካሜራ ፊት ሌላ፣ በመደበኛ ህይወት ሌላ መሆን የለብንም ብዬ ነው የማምነው።› የምትለው አስቴር ሚዲያ ላይ ስትቀርብ እንደሌሎች የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎች ከቀረፃ 2 ሰዓት በፊት ፀጉር ቤት አልያም  ከልብስ ዲዛይነር ጋር  ጊዜያዋን አታጠፋም፤ ይልቁንም ‹ሚዲያ ላይ ስቀርብ አንዳች የተቀባባ ሜካፕም ሆነ ማስመሰል የለብኝም። ለዝነጣም ብዬ መከራዬን አላይም። ሰዎች ሀሳቤን እንጂ አልባሳትና ሜካፕ ቁሳቁስ ምናምን ላይ እንዲያተኩሩ አልፈልግም። ከካሜራ ውጭ እንደምናወራው ማውራት አለብን ብዬ ስለማስብ እንደወረደ ሳልቀባባው ነው የማቀርበው። የሚዲያ ፐርሰናሊቲ ምናምን እያልን ያልሆነውን ሆነን እያሳየን ለምን ሰው እናሳስታለን።› ትላለች፡፡

<ትግራይ:- ምርጫውን ለማስቆም የሚተላለፍ ውሳኔ የጦርነት አዋጅ ነው – የትግራይ ክልል>

አስቴር ለውጡን ተከትሎ በሀገሪቱ እየተከወኑ ባሉ ነገሮች በላይ ለሀገሯ ተስፋ ታደርጋለች፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት እንደጠዋት ጤዛ ብቅ ብሎ ፀሐይ ስትወጣ ተኖ የሚጠፋ ያለመሆኑን በየተገኘችበ አጋጣሚ ሁሉ የምትናገር ነች ፤ባሳለፍነው ኣማት በዴስቲ ኢትዮጵያ በተዘጋጀውና ኢትዮጵያ የተስፋ ዘመኗን ለማዋለድ ከተዋቀረው የ50 እውቅ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች መሀከል አንዷ ሆናም ሀሳብ ስታዋጣ ነበር ፤‹አይዞሽ ሀገሬ አንቺ የፖለቲከኞች ብቻ አይደለሽም። በዚህ ፈታኝ ሰዓት ህግ እየጠቀሱ አጣብቂኝ ውስጥ እንደወደቅሽ ቢነግሩንም፤ ሞት እየደገሱ ቀነ ቀጠሮ ቢቆርጡም፤ የሚጠብቅሽ አይተኛም አያንቀላፋም። እምዬ ኢትዮጵያ እመኚኝ አንቺ ምንም አትሆኝም። የእውነት የሚወዱሽ፣ ለጥቅማቸው ሳይሆን ለጥቅምሽ Yሚሰውልሽ፣ ክብራቸውን ጥለው ለክብርሽ የሚቆሙልሽ፣ እውነተኛ ልጆች አሉሽ። ሀገር የፖለቲከኞች ብቻ አይደለችም።› ትላለች፡፡

አንዳንዴ አስቴር እጃችንን ወደ ሌሎች ሰዎች  ከመቀሰራችን በፊት ራሳችንን መጠየቅ እንዳለብን ትናገራለች፤‹ የሀገሬን ሰው ምን ነካው? ምን ዓይነት መሪ ነው የምንፈልገው? እኛስ ምን ዓይነት ተመሪ (ህዝብ) ነን? ፍፁም ንፁህ፣ ፅድት የለ፣ እውነተኛ፣ ጀግና፣ ምህረት አድራጊ፣ ምሁር፣ ብልህ፣ ሁሉን አወቅ፣ 100% እንከን አልባ? ሆሆሆ እንደዚህ አይነት መሪ በየትኛውም ሀገር የለም ሊኖርም አይችልም። ምርጫ ተካሂዶ እንኳን በአብዛኛው ህዝብ የመረጠው መሪ ቢነግስ ላልመረጡት ህዝቦች ጠላታቸው ነው። ፍፁም ህዝብ እንደሌለ ሁሉ ፍፁም መሪም የለም፤ ፍፅምና በምድር ገዢዎች ዘንድ መቼም አይመጣም።› በማለት ራሳችንን ወደ ውስጥ እንድንመለከት ታሳስባለች፡፡ አስቴር ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከፍ ያለ ክብር አላት፤ ዋጋ ተከፍሎበት የመጣ መሆኑን በማስተጋባትም ያለ ህዝቦች ምክክርና ውሳኔ በሰንደቅ አላማው መሀል ላይ የተደረገውን አርማ እንዲነሳ አቋሟ በማያሻማ ቋንቋ አቅርባለች፤‹ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሰንደቅ ዓላማችንን ለዘመናት ከታሰረችበት እናስፈታት፤ አሁን አዲስ ለውጥ በማየታችን ተስፋችን አንሰራርቷል፡፡ብዙ አስረኞች ተፈተው ደስ ብሎናል፤ ሰንደቃችን ግን እንዳትውለበለብ በህግ ታስራለች። ሀገር ካልተፈታች እስረኞች ቢፈቱ ከትንሽ እስር ቤት ወደ ትልቅ እስር ቤት እንደተዛወሩ ነው የሚቆጠረው፡፡የአፍሪካ ህዝብ የነፃነት አርማ፤ አንድ የነበረችው የታላቋ ኢትዮጵያ የአንድነት አርማ፤ የሀገር ወዳድ ዜጎች መኩሪያ ንፁኃ ባንዲራችንን ከታሰረችበት እናስፈታት፡፡ደስታችን መሉ ይሁን፡፡›   ትላለች፡ ፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe