‹የዓመቱ ምርጦች› ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ

በኢትዮጵያ ግዙፍ የመንግስት የልማት ድርጅት ከሆኑት ተቋማት መሀከል አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሎኮምን ላለፉት ሶስት ዓመታት በመምራት ከፍተኛ  ለውጦችን እያስመዘገቡ ያሉት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ድርጁቱን ከዚህ በፊት ከመሩ የስራ ሀላፊዎች መሀከል በዕድሜ ትንሷ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ አዲስ አበባ ተወልድ ያደጉት ወ/ሪ ፍሬህይወት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተም  ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከእንግሊዝ ሀገር ኦፕን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድምንስትሬሽን ተቀብለዋል፡፡

ወ/ሪት ፍሬሕይወት ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚነት ከመምጣታቸው በፊት በድርጅቱ ውስጥ በተለያዩ የስራ ሀላፊነቶች ለአምስት ዓመታት ያህል ማገልገላቸው ይነገራል፤ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን ከለቀቁ በኋላ  ዶክሳ ኤቲ የተባለ የአይቲ የግል ድርጅት አቋቁመው በዋና ስራ አስኪያጅነት ሲሰሩ ቆይተዋ፡፡ በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው የለውጥ ሀይል ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ወደ እዚህ ከፍተኛ የአስተዳደር ስልጣን ከመጡ ወጣት የስራ መሪዎች መሀከል አንዱ የሆኑት ወ/ሪፍሬሕይወት የኢትዮ ቴሌኮምን የመምራት  ሀላፊነት እንደተረከቡ ከእሳቸው በፊት ከነበሩት አቶ አንዱአለም አድማሴ ጋር ሃላፊነት ወንበር ላይ  የነበሩ 40 ያህል የስራ መሪዎችን ቀይረው ነው ስራ የጀመሩት፡፡

እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት መጀመሪያ ላይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በመቀሌ በሀገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ላይ የህወሃ ሀይሎች የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ በርካታ መሠረት ልማቶች ወድመዋል፡፡ ከእነዚህ መሠረተ ልማቶች መሀከል አንዱ የሆነው የኢት ቴሌኮም የሰሜን ሪጅን የግንኙነት መስመሮች ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን ተከትሎ በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶ ነበር፡፡

አገልግሎቱ በመቀሌ፤ በአዲስግራት፤ በሽሬ፤ በአድዋና በአክሱም ፤ በሰሜን ጎንደር ሪጅን  በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በማይካድራ፣ በቱርካ፣ በማይፀብሪ፣ እንዲሁም  በኮረም ያሉ የኢትዮ ቴሌኮም የግንኙነት መስመሮች ተበጣጥሰው ነበር አልያም ወድመዋል፤

ከዚህምበተጨማሪ  በትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ  ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በተደረገው  ጦርነት፣ ወቅት፣ በአገሪቱ ከ39.8 ቢሊዮን በላይ የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረው እንደነበር ተቋሙ አስታወቋል፤ እነዚህ ጥቃቶች የአገልግሎት ክልከላ (Disturbed Denial of Service /DDOS) ያልተፈቀደ መረጃን ለማግኘት መሞከር (Unauthorized Access) መሆናቸው ወ/ሪት ፍሬሕይወት አስታውቀው ነበር፡፡

የፌደራል መንግስት በወሰደው አስቸኳይ እርምጃ መቀሌንና አካባቢዋን ከተቆጣጠረ በኋላ የስልክ መስመሮችን መጠገንና ወደ ስራ የማስገባት ሃላፊነት የተጣለው በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩና በድርጅቱ ሰራተኞች ትከሻ ላይ ነበር፡፡ ወ/ሪት ፍሬህይወት የግንኙነት መስመሩን መጠገን ከመጀመራቸው በፊት በወቅቱ  የቴሌ መስመሮች ሲበጣጠሱና ሲቃጠሉ በስውር ካሜራ ጭምር የተቀረፁ ዝርፊያዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፤ መሠረተ ልማቱ የጠላት ሃገር ይመስል የደረሰበት ጉዳት መጠን ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ተመልሶ ይጠገናል ወይ; የሚል ጥያቄ የብዙዎች ነበር፤ በመሬት ላይ የተዘረጉ የፋይበር ገመዶች (OPGW) ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት አጋጥሟል፤ መስመሮቹን ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ይህንን የግንኙነት መስመር ጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት ሌት ከቀን መስራት የጀመሩት ወዲውኑ ነበር፡፡የድርጅቱን ሠራተኞችን በማሰማራት በአጭር ጊዜ ውስጥ የተበጣጠሱ የቴሌኮም አግልግሎቶች ወደ ስራ እንዲገቡ አድርገው ነበር፤

ያም ሆኖ ‹ተጠናቋል› የተባለው ጦርነት መልሶ በማገርሸቱ ብቻ ሳይሆን መሠረተ ልማቱን ለመጠገን ወደ ተለያ ቦታዎች የሚሰራማሩ የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች ላይ  ታጣቂዎች እርምጃ መውሰድ በመጀመራቸው የጥገና ስራውን አዳጋች ማድረጉ ታይቷል፡፡የጥገና ሰራተኞች  ለጥቃት እየተጋለጡ እንኳ  ‹ህዝቡ ከመሀል ሀገር ሰው ጋር ሊኖረው የሚገባው ግንኙነት መቋረጥ የለበትም› በሚል እምነት የጥገና ስራው እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡ ወ/ሪት ፍሬህይወት ምንም እንኳ ለጥገና የላኳቸው ሰራተኞቻቻው የህይወት መስዋእትነት ጭምር እየከፈሉ የጠገኗቸው መሠረተ ልማቶች ለህዝቡ አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ በጦርነቱ መውደሙ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞችን መስዋዕትነት  ዋጋ ከማሳጣትም አልፎ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከ እስከ ከ ተብሎ የሚጠቀስ እንዳልሆነ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይናገራሉ፡፡

ከለውጡ ጋር ተያይዞ በአመራሩ ጠንካራ ውሳኔ ከታየባቸው የፕራይቬታይዜሽን ሂደቶች መሀከል አንዱና ምናልባትም ግዙፉ ሊባል የሚችለው 40 ከመቶ የሚሆነውን የኢትዮ ቴሌኮም ድርሻን ወደ ግል ባለሀብቶች የማዛወር ሂደት ገና ከጅማሬው  ኢኮኖሚስቶችንና  የፖለቲካ ሰዎችን ጭምር ያከራከረ ጉዳይ ነው፡፡ ለዓመታት ለውጭ ሃለሀብቶች ዝግ የነበረው የቴሌኮም ዘርፍ በሩን ገርበብ አድርጎም ቢሆን ለመክፈት መወሰኑ  የዋና ስራ አስፈፃሚዋን ተወዳዳሪነት የሚፈትን መሆኑ እሙን ነው፡፡

የመንግስትን ውሳኔ ተከትሎም ባለፈው ታህሳስ ጨረታውን አሸንፈው ወደ ስራ እንዲገቡ የተፈቀደላቸውን ሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተሮችን በተመለከተ ብዙዎች ለኢትዮ ቴሌኮም እንደ ስጋት ምንጭ አድርው ሲጠቅሱ ታይቷል፡፡ ‹ የውጭ ተዋንያኖች መግባት ፈተና ብቻ ሳይሆን መልካም አጋጣሚም እንደሆነ ገምግመናል› የሚሉት  ወ/ሪት ፍሬሕይወት፣ ኢትዮ ቴሌኮም ያሉትን የቴሌኮሙዩኒኬሽን መሠረተ ልማት ለሚገቡት ኩባንያዎች በማከራየት ከፍተኛ ገቢ ለመሰብሰብ እንደሚችል በጥናት መረጋገጡን በመግለፅ በራስ መተማመናቸውን ከወዲሁ ማሳየት ጀምረዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ምሰሶዎችና ፋይበር መስመሮች በማከራየት ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት የውድድር ፈተናውን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር እየተዘጋጀ ነው፡፡

መንግሥት እያካሄደ ባለው ብሔራዊ የቴሌኮም የለውጥ ትግበራ አማካይነት ከቴሌ ፈቃድ ከወሰዱ  ሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያዎች መሠረተ ልማት በማከራየት ብቻ  ከ1.6 እስከ 1.8 ቢሊዮን ዶላር በዓመት  ለማግኘት አቅዷል፡፡  ገቢው የሚሰበሰበው ኢትዮ ቴሌኮም ካሉት  7,213 የሞባይል ምሰሶዎችና 22,000 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር  ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም 40 ከመቶ ድርሻውን ለውጭ ኩባንያዎች በመሸጡ የተገኘው 850 ሚሊዮን ዶላር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ከመቅረፉም በላይ ኩባንያው የአገልግሎት ጥራትና በደንበኞች አገልግሎት ላይ ከፍተኛ መሻሻል ለማሳየት ከፊሉ የሽያጭ ገንዘብ መንግስት ለኩባንያው ሊሰጥ እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች  ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ይህም  በኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ፣ ለጥገና ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ አፋጣን በማድረግ በኩል እመርታ ሊመዘገብ ይችላል ተብሏል፡፡

<‹የዓመቱ ምርጦች› ዶ/ር ሰላሜነሽ ጽጌ>

ኢትዮ ቴሌኮም በያዝነው ዓመት ካስጀመራቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ‹ቴሌ ብር› የተሰኘው በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ገንዘብ የማስተላለፊያ መላ በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ የሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞቹን ከ50 ሚሊዮን በላይ ለማድረስ የቻለው በወ/ሪት ፍሬሕይወት የሚመራው ኩባንያው ሞባይል ያላቸው ሰዎች ሁሉ ቴሌ ብር በተሰኘው ቀልጣፋ የገንዘብ ማዘዋወሪያና ግብይት መፈጸሚያ መተግበሪያ ብዙዎች እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ይህ ቴሌ ብር ይፋ በተደረገበት መድረክ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ‹ቴሌ ከፊል ድርሻውን ለውጭ ኩባንያዎች ቢያካፍልም እንደ ወትሮው የገበያው መሪ ሆኖ ለመቀጠል እንደሚችል አዳዲስ የሚያስተዋውቃቸው አግልግሎቶች ማሳያዎች ናቸው › ያሉ ሲሆን ቴሌ ይህን አገልግሎት መጀመር ከነበረበት 12 ዓመት መዘግየቱን ተናግረዋል፤ ቴሌ በሞባይል አማካይነት ገንዘብ የማስተላለፍ ፍቃድ እንዲሰጠው ተጠንቶ ለመንግስት የቀረበው ከ12 ዓመት በፊት እንደሆነ በማስታወስ፡፡ ቴሌ ብር በኢትዮጵያ 35 ከመቶ ብቻ የሆነውን የፋይናንስ አግልግሎት ተጠቃሚ  ተደራሽነት  ለማሳደግና የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን በመቀነስ ረገድ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የጎረቤት ሀገራትን ተሞክሮ በመጥቀስ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

የቴሌ ብር  አገልግሎት ገንዘብ ከማስተላለፍ፤ ከመቀበልና ክፍያ ከመፈፀም በተጨማሪ ከተለያዩ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ተሳስሯል፡፡ እንደ ውሃ ክፍያ፤ የኤሌትሪክ አገልግሎትና የትራንስፖርት ትኬት መቁረጥ እንዲሁም የትራፊክ ቅጣትን በዚሁ በቴሌ ብር መተግበሪያ መከወን ያስችላል ተብሏል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ብርን ባስተዋወቀ በሁለት ሳምንት ውስጥ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ የቴሌ ብር ተጠቃሚዎች ስምንት ሚሊየንን ተሻግሯል፡፡ በዚህም የቴሌ ብር የገንዘብ ዝውውር  ሂደት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው፡፡ከአራት ዓመታት በኋላ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ በቴሌ ብር በማንቀሳቀስ ገቢ ለማግኘት እንደሚችል ኢትዮ ቴሌኮም ያስጠናው ጥናት ያመለክታል፡፡የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት አንፃርም ባለፉት ሶስት ዓመታት በወር ይገኝ ከነበረው 5 ሚሊዮን ዶላር ወደ 20 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያሳድገው ታሳቢ ተደርጓል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፉ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ያለውን የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት የተቀላጠፈ ለማድረግ የዲጂታል ኦኮኖሚውን ከንግዱ እንቅስቃሴ ጋር የሚያስተሳስሩ የተለያዩ የማስፋፊያ ስራዎችን በዓመቱ ማከናወኑን ወ/ሪ ፍሬሕይወት ይናገራሉ፡፡ በዓመቱ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የ4ተኛው ትውልድ የኤልቲ ሞባይል አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎችን ለዚህ አብነት ናቸው፡፡

ዋና ስራ አስረፈፃሚዋ በዚህ ዓመት በተለያዩ ከተሞች እየተገኙ ስራ ካስጀመሯቸው የ4ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት ማስተናገጃ ማዕከላት መሀከል በደቡቡ ሪጂን ስድስት ከተሞችን በዋናነት ተጠቃሚ የሚያደገርው ማዕከልን በወላታ ሶዶ ከተማ ተገኝነተው ስራ አስጀምረዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ  ምዕራብ ሪጅን ያስጀመረው የ4ጂ ኤልቲኢ አገልግሎት  ወላይታ ሶዶ፣አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ፣ ቡታጅራና ጂንካ ከተሞች አገልግሎቱን ለማግኘት አስችሏቸዋል፡፡

< ‹የዓመቱ ምርጦች› ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገብረመድኀን>

በሰሜን ምዕራብ የአማራ ክልል ከተሞችም ተመሳሳይ የ4 ጂ የኢንተርኔት አገልግሎትን ተግባራዊ የተደረገው እየተጠናቀቀ ባለው ዓመት ሲሆን በክልሉ  ከሚገኙ 526 ማዕከላት ውስጥ በ74ቱ ማዕከላት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ ነው፡፡ ይፋ የተደረገው ይህ የፈጣን ኢንተርኔት አገልግሎት በባህር ዳር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ቡሬ፣ ዳንግላ፣ ቻግኒ፣ እንጅባራና ፍኖተ ሰላም አካባቢ የሚገኙት ከ746,000 በላይ ደንበኞች ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ተናግረዋል፡፡ በማዕከላዊ ምዕራብንም ሪጅን አምስት ከተሞችን በአምቦ፣ ሰበታ፣ ቡራዩ፣ ሆለታ እና ወሊሶ  የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀምሯል፡፡ሀገሪቱ ጦርነት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ዜጎችን እርስ በእርስ በቴሌኮም ለማገናኘትና ለማስተሳሰር እያደረጉት ያለው ጥረት  ድርጅቱን በስኬት ጎዳና ላይ እንዲጓዝ አድርጎታል፡፡

የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግም በኩባንያው ከተወሰዱ በርካታ ማሻሻያዎች ውስጥ አንዱ የታሪፍ ቅናሽ ማድረግ አንዱ ሲሆን በቅርቡም የሞባይል እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን የሚበረታታ ቅናሽ ተደርጓል፤ ማበረታቻው ብዙ አውርቶ ጥቂት መክፈልን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን በደቂቃ እስከ 35 ሳንቲም የሚደርስ ክናሽን አካቷል፡፡

በወ/ሪት ፍሬሕይወት የሚመራው ኢትዮ ቴሌኮም ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማቀድና በማስፈፀም በኩልም አቅደሙን በከፍተኛ ደረጃ እያሳየ ነው፡፡ በዚህ ባለው ዓመት ታቅዶ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የኔትወርክ መሠረተ ልማት  የ‹‹ሞጁላር መረጃ ማዕከል›› በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ማዕከሉ  150 ሚሊዮን ብር የወጣበት ሲሆን  በከፍተኛ ደረጃ የኃይል ፍጆታን የሚቀንስ፣ በቀላሉ ፍላጎትን ተከትሎ ሊስፋፋ የሚችልና ፈጣን የሲስተም ተከላ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል፡፡ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ማዕከሉን መርቀው በይፋ ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት፣ ‹እየጨመረ ላለው የግልና የመንግሥት ተቋማት የመረጃ ክምችትና ሥርጭት፣ ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ ማዕከል መገንባት አስፈላጊ ነው፤›ማለታቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ኩባንያው 80 ሚሊዮን ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው ፣ 41,800 የጥሪ ልውውጦችን በሰከንድ መቀበል የሚችልና እንዲሁም 2.7 ቢሊዮን የጥሪ፣ የዳታ እና የአጭር መልዕክት መረጃዎችን በየቀኑ ተቀብሎ የሚያሳልጥ ደረጃውን የጠበቀ የቀጣይ ትውልድ ቢዝነስ ሳፖርት ሲሰተም ተግባራዊ ማድረጉን ይፋ አድርጓል፡፡በተግባር ላይ የዋለው ሲስተም ዘመናዊውን የክላውድ ስርዓት ተከትሎ የተገነባ መሆኑ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን አጎልብቶ በፍጥነት ወደ ገበያ ለማድረስ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ከልማት ስራዎቹ ጎን ለጎንም በልዩ ልዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸውና ማህበረሰብ ተኮር አገልግሎቶች  ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኑን ተግባሩ ያሳያል ፡፡ እንደ አብነትም ለመቄዶኒያና ለሌሎች የበጎ አድራጎት ድርጅቶች መርጃ  የገቢ ማሰባሰቢያ ነፃ መስመር ከመፍቀድ  በተጨማሪ ከልማታዊው ትርፍ ላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፤ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ እንደሚናገሩት  ከኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ  ለግድቡ ፕሮጀክት በሦስተኛ ዙር ከደንበኞች በ8100 የጽሑፍ መልዕክት ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ  የ122.5 ሚሊዮን ብር ሰብስቧል፡፡ ይህ ገንዘብ የተሰበሰባው 1.3 ሚሊዮን ከሚደርሱ ደንበኞቹ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉን ለህዳሴ ግድብ  ሕዝባዊ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አስረክበዋል፡፡

የታታሪነትና የትጋት ተምሳሌት ተደርገው በብዙዎች ዘንድ የሚታመኑት ወ/ሪት ፍሬሕይወት በ2013 በጀት ዓመት 56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ያገኙ ሲሆን በ2014 በጀት ዓመት 70 ቢሊየን ብር ገቢ ለማስገባት እንዲሁም 175 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት አቅደዋል፡፡  በቀጣዩ ዓመትም ኢትዮ ቴሌኮም የ5G Advanced የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስጀመር እቅድ መነደፉን   ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ይፋ አድርገዋል።

ይህንኑ ትጋታቸውን መሠረት በማድረግ ቁም ነገር መፅሔት ወ/ሪት ፍሬሕይወትን የ2013 ዓ.ም ምርጥ የስራ መሪ ብላቸዋለች፡፡

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe