የዓመቱ ምርጦች – ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ

ትውልድና ዕድገቷል ወሎ  ነው፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘችው መዓዛ በምህርነት ለተወሰኑ ዓመታት ሰርታለች፤ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ከሚያሳስባቸውና ኢትዮጵያዊ ማንነት ያላቸው ሰዎች አንገት መድፋ ያስቆጫት ስለነበር የቀድሞው ሰማያዊ ፖርቲ ውስጥ ገብታ ታግላለች፤ ይህም የሀገራችን የፖለቲካ ሂደት ምን እንደሚመስልና የፖለቲካ ሀይሎችን አሰላላፍ በድንብ እንድትረዳ አስሏታል፡፡ መዓዛ በአሁኑ ወቅት በአባይ ሚዲያ ላይ በምታቀርባቸው ዝግጅቶችና በምታነጋግራቸው ለፖለቲካ ሰዎች በምታነሳቸው ሞጋች ጥያቄዎች ትታወቃለች፤ በተለይም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከስሩ ለመናድና የአክራሪ ብሔርተኝትን አጀንዳቸው ያደረጉ የፖለቲካ ሰዎችን ከፋፋፋይ ሀሳብ ተመልካቹ በደንብ አንዲረዳ ማድረጓን ብዙዎች ያምናሉ፤ ከልጅነቷ ጀምሮ ለሰው ልጆች እኩልነትና ሰብዓዊ ክብር እንዲኖራት ተኮትኩታ ማደጓ ምናልባት ከዘርኝነት ለፀዳ አመለካከትና የሀሳብ ሙግት እንድታደርግ በር አሳይከፍትላት እንዳቀረ ይታመናል፡፡

<ታዋቂ ሰዎች ዕርምጃ እንዲወሰድባቸውና ንፁኃን እንዲታፈኑ አቶ ጃዋር መሐመድ ትዕዛዝ መስጠቱን…>

የቅርብ ጓደኛዋ መንበረ ካሳዬ ‹መዓዛን የማውቃት በቀድሞ ሰማያዊ ፓርቲ በኢ/ር ይልቃል ጌትነት በሚመራበት ወቅት ፣ በሰላማዊ ትግል ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ደፋ ቀና ስትል ነበር ። መዓዛ ሀገር ወዳድ፣ ጭቆና የምትጠላ ፣ ለሰብዓዊነት መብት የቆመች ብርቱ ሴት ናት ።› በማለት ትገልጻታለች፡፡ መዓዛ የአንድ ሰሞን የፖለቲካ ማሟያ ዜና ሆነው ስለጠፉት የዶምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ታማሪዎች ጉዳይ እንደ ወላጅ፤ እንደ አሳዳጊና ሀላፊነት እንደሚሰማው የሚዲያ ሰው ሆና በተደጋጋሚ ጉዳዩን ፕሮግራም ሰርታበታለች፤ ሰሞኑንም ይህንኑ ጉዳይ የውይይት አጀንዳ በማድረግ መንግስት ስለጠፉት ተማሪዎች ጉዳይ በሀዘን ተቆራምደው በተስፋ ለሚጠባበቁት ወላጆች ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ፕሮግራም በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዘጋጅታ ነበር፤ ሆኖም ስብሰባና የፖለቲካ ፖርቲ ድርጅቶች መግለጫ በፖሊስ መከልከል አዲስ ባልሆነባት አዲስ አበባ የሚዲያ ውይይትም ፍቃድ የለውም በሚል መከልክሉን መዓዛ በፌስ ቡክ ገፆ ላይ ‹ የአብይ አህመድ መንግስት እያለ የታገቱ 17ተማሪዎች ጉዳይ እልባት እንደማያገኝ አረጋግጫለሁ!> በሚል ርዕስ እንዲህ ብላለች፤ ‹ከታገቱ 270ኛ ቀን መሆኑን በማስመልከት የሚመለከታቸው አካላትን ለማሳሰብ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል የፓናል ውይይት ማዘጋጀታችንን መግለፄ ይታወቃል። ለውይይቱ የአዳራሽ ኪራይ ከሶስት ቀናት በፊት የከፈልንና ከሆቴሉ ጋርም ውል ፈፅመን የነበረ ቢሆንም ሆቴሉ ዝግጅቱ እንዲሰርዝ በአዲስ አበባ ፖሊስ ታዝዣለሁ በማለት ውሉን ማቋረጡን አሁን በስልክ አሳውቆኛል። በዚህ መሰረት የነገውን ውይይት እና የመታሰቢያ ፕሮግራም ማካሄድ አለመቻላችንን እገልፃለው።›

የታገቱ ተማሪዎቻችንን ለማሰብ እና ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ የሚዲያ ውይይት ለማድረግ የመንግስት ፈቃድ አስፈላጊ እንዳልሆነ የምታምነው መዓዛ ውይይቱን በማንኛውም መልኩ ለማድረግና ለህዝብ በማድረስና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ለማንቃት እንደሚሰራ ትናገራለች፤ መዓዛ በቅርቡ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ስቱዲዮ ተቀምጣ በመተንተን ብቻ አልተወሰነችም፤ የጋዜጠኝነት ሙያ የደረሰውን መረጃ እንዳለ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን የመረጃውን ትክክልኛነት እቦታው ድረስ ሄዶ በመመልክት መሆኑን በመረዳት የስቱዲዮ መሣሪያዎቿን ይዛ እቦታው ድረስ ሄዳ በመመልከትና ተጎጂዎችን በማነጋገር እውነቱን ለህዝብ አቅርባለች፤ ‹የንፁሀኑን ሰቆቃ የግፈኞቹን ጭካኔ አርሲ፣ባሌና ምዕራብ አርሲ ከባልደረቦቼ ጋር በቦታው ተገኝቼ ተመለከትኩ፤ ሁሉም ነገር ከአእምሮ በላይ ነው።› ብላለች፡፡

<በአዲስ አበባ ሕገወጥ የመሬት ወረራ የወጣው ሪፖርት “ሃሰተኛ” ነው- የቀድሞው ምክትል…>

በዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ህይወታቸውን ካጡ ዜጎች መሀከል የአንዱ ታሪክ ‹ይሄን ባልፅፈው ባታይዩትና እንደእኔ ባትታመሙ ደስ ይለኝ ነበር ፤ግን ደሞ ቃሌ ነው! › በማለት ታሪኩን እንዲህ አጋርታለች፤ ‹ብርሃኑ ዝቅአርጋቸው ተወልዶ ያደገው አርሲ ነው፤የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሲሆን ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ መምህር ነው፤ የአራት ሴትና አንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆን በጭሮ ከተማ ከ30አመት በላይ ቤተሰብ መስርቶ ንብረት አፍርቶ ይኖር የነበረ ነው። ብርሃኑ ዝቅአርጋቸው በምእራብ ሃረርጌ በአራጆች በግፍ አገዳደል በድንጋይ፣ በሜጫ፣ በአጠና ተደብድቦ ነው የተገደለው። ሬሳውን እስከ ቀኑ 10:00ሰአት ድረስ እንዳይነሳ በመከልከል አስከሬኑ ስር ቁጭ ብለው ጫት ሲቅሙ ከዋሉ በኋላ መከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ከተቆጣጠረ በኋላ ሄዶ አስከሬኑን በማምጣት መኖርያ ቤቱ ስለወደመ ከተማው ውስጥ በሚገኝ በታላቅ እህቱ ቤት እንዲያርፍ አድርጎአል። በማግስቱም ከከተማው ውጭ በሚገኘው በአጥቢያው በእግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስትያን ሬሳው እንዳይቀበር ጽንፈኞቹ በመከልከላቸው በከተማ ውስጥ ባለችው በደብረ ጽዮን ቅድስት ልደታ ማርያም ቤተክርስቲያን እንዲቀበር ሁኗል።› ትላለች፤

ይሄ የመዓዛ ዘገባ ለህዝብ መድረሱ ምቾት የሚነሳቸው አካላት የመዓዛን የአደባባይ ሙግት በማስፈራራት ለማስቆም መሞከራቸው አልቀረም፤ ‹ከእናንተ ጩኸት እና ማስፈራሪያ በላይ በአይኔ ያየሁት እና በጆሮዬ የሰማሁት ሰቆቃ ከአዕምሮዬ አይጠፋምና በጭራሽ ዝም አልልም፤ ድምፅ ልሆናቸው ቃሌ ነው!! ሞት እንደሆነ ዝም ብለው ቤታቸው ለተቀመጡትም አልቀረ!!› ስትል ነው አቋሟን ያሳወቀችው፤

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe