የዓመቱ ዜና እረፍት ጋዜጠኛ መልካሙ ደምሴ

በሚድያው ዓለም ከ30ዓመት በላይ ያገለገለው መልካሙ ደምሴ ታህሣሥ 10፣2016 ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ላለፉት 22 ዓመታት መኖሪያውን በአትላንታ አሜሪካ ያደረገው መልካሙ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በ 120 ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢነት ያገለገለ ሲሆን በጠቅላላ በኢቢሲ ለ 10 ዓመት በሙያው ሠርቷል።

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ከሶቭየት ህብረት በማስተርስ የተመረቀው መልካሙ ትውልድ እና ዕድገቱ በአዲስ አበባ ልደታ ሰፈር ነበር።

ጋዜጠኛ መልካሙ ደምሴ መኖሪያውን በባህር ማዶ ካደረገ በኋላ በሚድያ ሥራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ ያደርግ ነበር ።

በተለይም በአድማስ ሬድዮ እና በድንቅ መጽሔት ላይ ትልቅ አሻራ ማኖሩ ይነገርለታል ።

ጋዜጠኛ መልካሙ ባለ ትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር ።

የጋዜጠኛ መልካሙ ደምሴ የቀብር ሥነ ስርዓት ቅዳሜ ታህሳስ 13፣2016 በአሜሪካ በ11am በደብረብስራት ገብርኤል ፀሎት ከተደረገ በኋላ በ12:30-1pm ቀብሩ ተፈፀማል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe