በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ25 ዓመታት ያገለገለችው ጋዜጠኛ ዓይናለም ባልቻ ከእናቷ አያልነሽ ትዛዙደ፣ ከአባቷ ባልቻ ወንድሙ በ1961 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደች፡፡ ጋዜጠኛ አይናለም እድሜዋ ለትምህርት ሲደርስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በበየነ መርዕድ የህፃናት አምባ ተከታትላለች። በመቀጠል የቡልጋሪያ መንግስት በሰጣት የትምህርት እድል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን አጠናቃ ሶፊያ ዩንቨርሲቲ በመግባት በጋዜጠኝነትና በህዝብ ግንኙነት ሁለተኛ ዲግሪዋን ሰርታለች።
ጋዜጠኛ አይናለም ባልቻ በቡልጋሪያ ቆይታዋን አጠናቃ በ1988 ዓ.ም ወደ ሃገሯ ኢትዮጵያ በመመለስ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለተወሰነ ጊዜ ሰርታለች።
ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሪፖርተርነት ከዚያም በህፃናት ዝግጅት ክፍል በአዘጋጅነት ስታገለግል ቆይታለች።
የህፃናት ክፍሉ የህፃናትና ታዳጊዎች ተብሎ ሲደራጅ በዳሬክተርነት ስትመራ ነበር። ይሁንና በድንገት ባጋጠማት የጤና እክል ላለፉት ሦስት ዓመታት የህክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታ ታህሳስ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በ55 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች።
ጋዜጠኛ አይናለም ባልቻ የአንድ ሴት ልጅና የሁለት የልጅ ልጅ እናት ነበረች።

