የዛምቢው ፕሬዜዳንት ሚኒስትሮች በካቢኔ ስብሰባ ወቅት መተኛት እንዲያቆሙ አስጠነቀቁ፡፡
ፕሬዜዳንት ሃካንዴ ሂቺሌማ በስብሰባ ወቅት የሚያንቀላፉ ሚኒስትሮች ቸልተኞች እና ራሳቸውን መቆጣጠር የተሳናቸው መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሮች ምሽቱን የት እያሳለፉ ነው በስብሰባ ወቅት የሚያንቀላፉት ይህ ለእኔ ወንጅል ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
የፕሬዜዳንቱን ንግግርም የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሚኒስትሮቹ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት እና የምሽት ድግሶችን ታበዛላችሁ ለማለት ፈልገው እያሉ ለንግግራቸው ትርጉም ሲሰጡት ተሰተውሏል፡፡ ምንም እንኳን እሳቸው በቀጥታ ይህንን ባይሉትም፡፡
ፕሬዜዳንቱ ዝቅተኛ የስራ አፈጻጸም ያላቸውን ሚኒስትሮችን ከስራ በማሰናብትም ይታወቃሉ ተብሏል፡፡

