የዩክሬን ፕሬዝዳንት በዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ንግግር ለማድረግ ያቀረቡት ጥያቄ ፊፋ ውድቅ አደረገ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚዬር ዘለንስኪ እሁድ በሚካሄደው የኳታር ዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ስለዓለም ሰላም ንግግር ለማድረግ ያቀረቡትን ጥያቄ ፊፋ ውድቅ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

የፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት በቪድዮ አማካኝነት ከጨዋታው በፊት በእስታዲየም ለሚገኙ ኳስ ደጋፊዎች መልእክት ለማስተላለፍ ያቀረበው ጥያቄ አሉታዊ ምላሽ በማግኘቱ አስገርሞኛል ብሏል፡፡

በዚህም በፕሬዝዳንቱና በፊፋ መካከል ውይይት እየተካሄደ መሆኑንና በፊፋ በኩል ምንም አስተያየት እንዳልተሰጠ ሲኤንኤን ምንጩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

በፊፋ ህግ መሰረት በንግግርም ሆነ በማንኛውም መንገድ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶች ማስተላለፍ የተከለከለ ነው።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጉዳዩ በማይገናኙ ታላላቅ የዓለም መድረኮች ጭምር በመጠቀም መልዕክታቸውን ለማስተላለፍ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe