ኪዳኔ ሃይሌ ፀባየ ሸጋ ቀልድና ጨዋታ አዋቂ፣ በኩናማ ዜማና ግጥም ድርሰት ከፊት የሚቀመጥ፣በተጨማሪም ድምፃዊና ሳክስፎኒስት ነበር።
ቤተሰቦቹን ጥየቃ ሸራሮ በሄደበት በአደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ መጋቢት 06 ቀን 2017 ዓ.ም. ሕይወቱ አልፏል።
ኤልያስ መልካ በቅንብር የተሸለመበትን የኩናምኛ ዘፈን ድርሰትን ግጥሙን የፃፈው፣ ዜማውን የደረሰውና በድምፅ ያቀነቀነው ኪዳኔ ነበር።
ድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ – “ኦማኒንዳ ጉዳ” በተሰኘው የኩናማ ሙዚቃው በበርካቶች ዘንድ ይታወቃል።
የድምጻዊ ኪዳኔ ኃይሌ የኩናማ ሙዚቃ ኤልያስ መልካ ካቀናበራቸዉ አልበሞች “ብፍቅሪ ሸፊተ” አልበም ውስጥ የሚገኝ ሙዚቃ ነው።
በ1956 ዓ.ም. የተወለደው ኪዳኔ ኃይሌ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
ሥርዓተ ቀብሩ ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 2: 00 ሰዓት ላይ ሸራሮ በሚገኘው በመድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
የድምፃዊና ሳክስፎኒስት ኪዳኔ ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

