የድምፃዊ ኬኔዲ መንገሻ ቆየት ያሉ ሙዚቃዎች በአዲስ መልክ ተሰርተዉ ለአድማጭ ሊቀርቡ ነዉ

የተወዳጁ ድምፃዊ ኬኔዲ መንገሻ ሙዚቃዎች ከሁለት አሰርት አመታት በኃላ በዳግም የሙዚቃ ቅንብር ተሰርተዉ ለአድማጭ የሚቀርቡት በእዉቁ የግጥም እና ዜማ ደራሲ አበበ መለሰ አማካኝነት ነዉ፡፡
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 መሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረገዉ አበበ መለሰ ለኬንዲ ድምፅ እና አዘፋፈን ቅርብ የሆነዉ ደምፃዊ እንዳለ አባተ የተመረጡ የኬኔዲ ዜማዎችን ተጫዉቷቸዋል፡፡
ኬኔዲ መንገሻ እንባ ስንቅ አይሆነኝ የተሰኘዉን የመጨረሻ አልበሙን የበዛ የግጥም እና የዜማ ስራዎቸን ከአበበ መለሰ ጋር የሰራ ሲሆን አሁን በዳግም የሙዚቃ ቅንብር የተሰሩት ሙዚቀዎችም የአበበ መለሰ የፈጠራ ስራዎች ሰለመሆነቸዉም ተነግሯል፡፡
ይህንን ስራ እንድጫወት በመመረጤ ደስተኛ ነን የሚለዉ የኬኔዲን ሙዚቃ የማዜም እድል ያገኘዉ ድምፃዊ እንዳለ አባተ በተሰጠዉ አደራ ልክ የድምጻዊዎን ከብር በሚመጠን መንገድ ሙዚቃዉን መጫወቱን ገልጧል፡፡
የሙሉ ባንድ ስሜት ኖሮት የተሰራዉን አልበም አሌክስ ይለፍ በቅንበር፤ሰለሞን ሀ/ማርያም በማስተሪንግ፤ጆቫኒ ሪኮ በቤዝ ጊታር ተሳትፈዉበታል፡፡
የሙዚቃ አልበሙ በቅርቡ ለአድምጭ እንደሚቀርብም ታውቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe