የጀርመን የቴክኖሎጂ ኩባንያ በዐይን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ይፋ አደረገ

በመተግበሪያው እስካሁን ከ70 ሺህ በላይ ሰዎችን መመርመር የተቻለ ሲሆን፤ 95 በመቶ ውጤታማ ነው።

የመመርመሪያ መተግበሪያው የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎችን በ3 ደቂቃ ውስጥ መለየት ያስችላል።

መቀመጫውን ሙኒክ ያደረገው የቴክኖሎጂ ኩባንያው ዐይንን ‘ስካን’ በማድረግ የኮሮና ቫይረስን መለየት የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አደረገ።

በመተግበሪያው አማካኝነት የኮሮና ቫይረስ ያለባቸው ሰዎችን በሶስት ደቂቃ ውስጥ መለየት ይቻላል ያለው ኩባንያው፤ በተደረገው ሙከራ 95 በመቶ ውጤታማ መሆኑንም አስታውቋል እንደ ሮይተርስ ዘገባ።

መተግበሪያውን የሰራው ሴሚክ አር.ኤፍ የተባለ ጀርመን የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው፡፡

ኩባንያው በአሁኑ ወቅትም ፈጠራውን ተግባር ላይ ለማዋል ከአስተዳዳሪ አካላት ፍቃድ በመጠበቅ ላይ ሲሆን፤ በአንድ ወር ውስጥ ጥቅም ላይ እንደሚውልም ይጠበቃል።

መተግበሪያው ለምርመራ በስማርት ስልክ የተነሳ ፎቶ የሚፈልግ ሲሆን፤ ፎቶግራፉን ስካን በማድረግ በአይን ውስጥ የሚፈጠረውን የማቃጠል ስሜት ተከትሎ የሚታየውን ‘ሐምራዊ’ ቀለም በመመልከት የሚለይ መሆኑም ታውቋል።

የኩባንያው ዋና ዳይሬክተር ዎልፍጋንግ ግራበር“ቫይረሱን ከ2 ሚሊየን ሐምራዊ የዐይን ቀለማት ሽፋን ውስጥ መለየት ችለናል” ብለዋል።

ዳይሬክተሩ በመተግበሪያው እስካሁን ከ70 ሺህ በላይ ሰዎችን መርምረናል ያሉ ሲሆን ቴክኖሎጂው በሰከንዶች ውስጥም በሚሊየን የሚቆጠሩ ስካኖችን የመለየት አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ መዋል ከቻለም እንደ እግር ኳስ ያሉ ብዙ ተመልካቾች የሚታደሙባቸው ሁነቶችን በቀላሉ ወደ ነበሩበት ለመመለስ ያስችላል ብለዋል።

ለምርመራውም በመተግበሪያው ሁለቱን ዐይናችንን ፎቶ ማንሳት እና ለምርመራ መላክ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የመርመራው ውጤትም በተመርማሪው ግለሰብ ስማርት ስልክ ላይ የሚላክ ይሆናል።

መተግበሪያው ለንግድ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ሰዎች በወር በ570 የአሜሪካ ዶላር ይቀርባል የተባለ ሲሆን፤ ከቆይታ በኋላም ግለሰቦች መጠቀም በሚችሉበት መልኩ እንደሚቀርብ ተነግሯል።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe