የ27 ጊዜ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ መፅሐፍ ተጻፈለት፡፡የአትሌት ኃይሌን የህይወትና የስራ ፍልስፍና የሚያስረዳውን መጽሀፍ የጻፈችው ልጁ ሜላት ኃይሌ ገብረስላሴ ናት፡፡
ረዳት ፀሐፊው ደግሞ አባዮሚ ሮቲማ የተባለ ፀሐፊ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በ12 ምዕራፍ ተከፋፍሎ የተዘጋጀውን መጻሐፍ ለማሰናዳት ሁለት ዓመት እንደፈጀ ፀሐፊዋ ተናግራለች፡፡
አትሌት ሃይሌ ብዙውን የህይወት ታሪኩን ህዝብ የሚውቀው ቢሆንም መጽሐፉ የሚያተኩረው የህይወትና የስራ ፍልስፍናው ላይ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
ለዚህም ጸሐፊዋ ልጁ እንደመሆኗ ከሌሎች ሰዎች በተለየ የአትሌት ሃይሌን ህይወት ለማወቅና ለመጻፍ እንዳስቻላት ገልጻለች፡፡
መጽሐፉ አትሌት ኃይሌ ከእድገቱ እስከ አሁን ባለው የሯጭነትና የቢዝነስ ምዕራፍ የተከተላቸውን አመለካከቶቹን፡ፍልስፍውን፡የህይወት ልምዱ የተካተተበት መሆኑን ሜላት ኃይሌ ገልጻለች፡፡
ለጊዜው Dissecting Haile በሚል ርዕስ ለህትመት የሚበቃው መጽሐፉ ወደፊት ወደ አማርኛና ወደ ሌሎች ቋንቋዎች እንደሚተረጎም ተነግሯል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሜላት የአባቷን የህይወት ታሪክ የሚመለከት ሌላ መጽሐፍ በማዘጋጀት ላይ እንደሆነችም ይፋ አድርጋለች፡፡//

