የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት የተሳተፉት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን ሰጡ

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የነበሩትና በጡረታ በክብር የተሰናበቱት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ እሻ እና ብርጋዴር ጄኔራል ሙሉጌታ በርሄ እጃቸውን በሰላም መስጠታቸውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ እጃቸውን የሰጡት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የጁንታውን ታጣቂ ሃይል በመምራትና በማዋጋት ላይ የነበሩ ናቸው።

መኮንኖቹ በጡረታ ከተገለሉ በኋላ ጁንታውን በመቀላቀል የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የህወሓት ጁንታ ጥቃት በፈጸመበት ወቅትም ዋና አስተባባሪ የነበሩ ናቸው።

አያይዘውም አሁን ላይ በርካታ የጽንፈኛው ቡድን ሚሊሻ ፣ ልዩ ሀይል እና የፖሊስ አባላት እጃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉም ብለዋል፡፡

እጃቸውን የሰጡ አባላትም በአግባቡ ህጋዊ ከለላ እየተሰጣቸው ወደ ህብረተሰቡ ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ም ነው ያሉት፡፡

ቀሪዎችም ጁንታው በማይወክላቸው ጦርነት ውስጥ የሚማግዳቸው ሀይሎች ይህንን ዕድል ተጠቅመው እጃቸውን ለመስጠት ፍላጎት ካሳዩ አሁንም በሩ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡

ሠራዊቱም ወንጀለኞችን የማሰስና የማደኑን ተግባር አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፥ በየጊዜው ቦታ እየቀያየሩ ከሚደበቁበት ዋሻ ውስጥ እየተለቀሙ በቁጥጥር ስር እስከሚውሉ ድረስ አደኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስረድተዋል፡፡

SourceFBC
Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe