የጃኪ ጎሲ ‹ባላምባራስ›አዲስ አልበም ለፋሲካ ሊወጣ ነው

የተወዳጁ ድምጻዊ ጃኪ  ጎሲ /ጎሳዬ ቀለሙ/ የመጀመሪያ አልበሙም ለፋሲካ እንደሚያወጣ ተሰማ፡፡

14 ዘፈኖችን  የያዘው የጃኪ አልበም አንድ የትግርኛና አንድ የኦሮሚኛ ዘፈኖችን የያዘ ሲሆን የአልበሙ መጠሪያ ‹ባላምባራስ› የሚል እንደሆነ ታውቋል፡፤

አልበሙን ጃኪ ለሪቮ መልቲ ሚዲያ በ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር መሸጡ የታወቀ ሲሆን ከአልበሙ ጋር ጃኪ አራት ኮንሰርቶችን ለሪቮ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡ ኮንሰርቶቹ በአዲስ አበባና በሶስት የተመረጡ ከተሞችን እንደሚካሄድ ተገልጧል፡፡

ጃኪ ጎሲ ከዚህ ቀድም ባወጣቸው ነጠላ ዜማዎች ከፍተኛ ተመልካች ያገኘ ድምጻዊ ሲሆን ፊያሜታ የተባለው ዘፈኑ ብቻ በዩቲዩብ ላይ ከ25 ሚሊየን በላይ ተመልካች እንዳገኘ ታውቋል፤

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe