የጃኮብ ዙማን እስር ተከትሎ በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰ አመጽ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 72 ደረሰ

ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ ሁከቱን ለማቆም የጸጥታ ኃይሎች ቢያሰማሩም አመጹን ለማስቆም እየተፈተኑ ነው፡፡

በአመጹ እስካሁን ከ1 ሺ 200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተገለጸው፡፡

5ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የደቡብ አፍሪካ ሁከት የ72 ሰዎች ህይወትን ከመቅጠፉ በዘለለ የተለያዩ መጋዘኖችና ግምጃ ቤቶች እንዲዘረፉም ምክንያት መሆኑን ተገለጸ፡፡

ፕሬዝዳንት ሲርል ራማፎሳ ሁከቱን ለማቆም የጸጥታ ኃይሎች ቢያሰማሩም አመጹን ለማስቆም እንደተፈተኑ ነው የፈረንሳዩ የዜና ወኪል (ኤ.ኤፍ.ፒ) መረጃ የሚያመላክተው፡፡

እስካሁን በሁለት አውራጃዎች በተፈጠረው ህገ-ወጥነት ከ 1,200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች አንድ የህብረተሰብ ሬዲዮ ጣቢያ በመዝረፍ እና ስርጭቱ እንዲያቋርጥ በማድረግ እንዲሁም አንዳንድ ኮቪድ-19 የክትባት ማዕከሎች በመዝጋት እና አስቸኳይ የሚያስፈልጉ ክትባቶችን በማስተጓጎል የተጠረጠሩ ናቸው፡፡

በጓተንግ እና በክዋዙሉ-ናታል አውራጃዎች ሰዎች ምግብን፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን፣ አረቄዎችን እና አልባሳትን ከመደብሮች ሲሰርቁ ከነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጋር በተፈጠረ ችግር በርካቶች እንደሞቱ የፖሊስ መኮንን ጄኔራል ማትፔሎ ፒተርስ ትላንት ምሽት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል ፡፡

የፖሊሰ መኮንን ጀነራሉ 27 ሰዎች ከክዋዙሉ-ናታል እንዲሁም 45 በጓተንግ አውራጃዎች መሞታቸውንና ለዚህም አስፈላጊውን ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኤ.ቲ.ኤም ማሽን ለማቃጠል ሁከት ፈጣሪዎች በወረወሩት ቦምብ ምክንያት በተፈጠረ ፍንዳታ ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች በተመለከተም ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ የፖሊስ መኮንኑ ተናግሯል፡፡

ረብሻው በሁለቱ አውራጃዎች በሚገኙ ከተሞች እተዛመተ እንደሆነም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡

ፖሊስ በበኩሉ ረብሻው ወደ ተቀሩት ሰባት አውራጃዎች ተዛምቶ ከባደ ቀውስ እንዳይፈጠር በተጠንቀቅ ተዘጋጅቻለሁ እያለ ነው፡፡

በችሎት መድፈር 15 የእስር ወራት የተላለፈባቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ እጄን ለፖሊስ እጅ አልሰጥም ሲሉ ከቆዩ በኋላ ሐሙስ ጠዋት እጅ መስጠታቸው ይታወሳል።

የ 79 ዓመቱ የቀድሞ የደቡብ አፍሪከ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ እስር ቤት መግባታቸው እንዲዘገይ ያቀረቡት ማመልከቻ በፒተርማርቲዝበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ዙማ በማረምያ ቤት እንዲቆዩ መደረጉንም ጭምር፡፡

ዙማ ካላፈው ሐሙስ አንስቶ የ 15 ወራት እስራታቸው ጀምረዋል፡፡

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe