የገቢዎች ሚኒስቴር ሁለት ኦዲተሮች 12 ሚሊዮን ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፤ 

ተጠርጣሪዎቹ የገቢዎች ሚኒስቴር የመካካለኛ ግብር ከፋዮች ከፍተኛ ኦዲተሮች ናቸው፤ ፍስሐ ዘውዴ ፍሌ እና  ዋጋሪ ደጉ ተርፉ ይባላሉ፤የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት ከፍተኛ ኦዲተር ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ሁዋ ጂያን የተባለ የቻይና ድርጅትን የ4 ዓመታት የታክስ ኢዲት እንዲሰሩ ተመድበው ነበር፤

  • ይህንኑ ተከትሎም ኦዲት ተደራጊው ድርጅት ከእህት ድርጅቶች በብድር የወሰደውን ገንዘብ ብድሩ በሕጋዊ አካል የፀደቀ አይደለም በመሆኑም እንደ ገቢ እንጂ እንደ ወጪ አይያዝም ይላሉ፤  በዚህም የድርጅቱ የታክስ ዕዳ 185,000,000 (አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሚሊዮን) ብር እንደሚሆን ለድርጅቱ ሀላፊዎች በመግለፅ ድርድር ይጀምራሉ ይላል አቃቤ ህግ፤
  • ነገር ግን 12,000,000 (አስራ ሁለት ሚሊዮን) ብር ለእነሱ የሚሰጣቸው ከሆነ ድርጅቱ ለመንግስት የሚከፍለውን የግብር እዳ ከ185,000,000 (አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሚሊዮን) ብር ወደ 4,900,000 (አራት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሺህ) ብር ዝቅ እንደሚያደርጉላቸው በስልክና በአካል ተገናኝተው ከተደራደሩ በኋላ ገንዘቡን ለመቀበል መስከረም 6 ቀን 2014 ከቀኑ 9፡30 ላይ ቫርኔሮ ሪል ስቴት አጠገብ ከሚገኘው ጋራለቡ ሆቴል ግቢ ውስጥ ይገናኛሉ፤
  • ቼኩን የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ይዘው ሲቀርቡ  ገንዘቡን ለመቀበል የተስማማነው በጥሬ እንጂ በቼክ  አይደለም ብለው ሲጨቃጨቁ  በፌዴራል ፖሊስ ክትትል አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ይላል አቃቤ ህግ፤በዚህም መሰረት ጉዳዩ የቀረበለት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ለመስጠት ለጥር 4 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe