የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷ ተሰማ

የገዛ ባሏን በመርዝ የገደለችው ተከሳሽ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቷን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ፡፡

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ አቶ ዋቁማ ጡሪ እንዳስታወቁት በነቀምቴ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ ውስጥ በምትኖረው ተከሳሽ ወይዘሮ እልፍነሽ በቀለ ጅራታ ላይውሳኔው የተላለፈው ባሏን አቶ አዳነ አሰፋውን በመርዝ መግደሏ በመረጋገጡ ነው።

ሟች ከኦሮሚያ ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር ከተበደሩት 86ሺህ ብር ውስጥ 10ሺህ ብር እንዲሰጣት ጠይቃ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ቂም ይዛ መርዝና አይብ በማደባለቅ መጋቢት 01/2011ዓ.ም ከምሽቱ በግምት አራት ሰዓት አካባቢ እንዲመገብ አድርጋለች።

ወደ መኝታ ክፍል እንደገባም በሩን በውጭ በኩል ዘግታ መሞቱን ካረጋገጠች በኋላ ራሱን በራሱ የገደለ ለማስመሰል ’’ፀፀት’’ ተብሎ የተፃፈና ሁለት ገጽ ያለው ወረቀት በደረቱ ላይ አስቀምጣ መኖሪያ ቤቱን በመዝጋት ንብረት ስታሸሽ መያዟን አመልክተዋል።

የተከሳሿ ድርጊት በዞኑ ዓቃቤ ሕግየሕግ ምሥክሮች በመረጋገጡ፣ ራሷም የፈጸመችውን ድርጊት ማመኗንና የመከላከያ ማስረጃም የለኝም ማለቷን አቶ ዋቁማ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በግንቦት 21/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሿ ሆን ብላ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት ተዘጋጅታ የፈጸመችው ድርጊት በመሆኑ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል ፡፡

የዞኑ ዓቃቤ ሕግ አቶ ፈየራ አበሹ በበኩላቸው “ተከሳሿ የፈጸመችውን ድርጊት በማመኗና ከዚህ በፊት ምንም ሪኮርድ የሌላት በመሆኑ የተወሰደባት እርምጃ በቂና አስተማሪ ነው” ብለዋል ፡፡ የዜና ዘገባው የኢዜአ ነው።

Kumneger Media
Kumneger Media
Kumneger Media is a News and Entertainment Website & Channel. Kumneger Media in addition to News and Entertainment it is the hub of Politics, Movies, Drama, Music, Comedy, Documentary and More!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe