የጉራጌ ሕዝብን የክልልነት ጥያቄ ባጭር ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ አገር ዓቀፍ ፓርቲ ተመሰረተ

ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትህ ፓርቲ አገር ዓቀፍ ፓርቲ ሆኖ ትናንት በአዲስ አበባ በይፋ ተመስርቷል።
ፓርቲው ትናንት ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ፣ የጉራጌ ሕዝብን የክልልነት ጥያቄ ባጭር ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ እና የጉራጌ ሕዝብ በአገሪቲ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መስኮች ጉልህ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ በርትቶ እንደሚሠራ ከምስረታው ቀደም ብሎ የምስረታ ኮሚቴው ለዋዜማ ተናግሯል።
ፓርቲው የምስረታ ጉባኤውን ያካሄደው፣ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ እውቅና ከሰጠው ከጥቂት ወራት በኋላ ነው። የፓርቲው መስራች ጉባኤ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱን የመረጠ ሲሆን፣ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብና የፖለቲካ ፕሮግራም አጽድቋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe