የጉግል ኩባንያ አድሰንስ አካውንት በኢትዮጵያ ስራ ካቆመ 9 ቀናት መቆጠራቸው ተነገረ

የጉግል ኩባንያ አንድ አካል የሆነው አድሰንስ አካውንት ባልታወቀ ምክንያት በኢትዮጽያ ስራ ካቆመ 9ቀናት መቆጠራቸው ተነገረ።

አድሰንስ አካውንት አንድ ግለሰብ ወይም ተቋም የዩትዩብ አካውንት ሲከፍት የዩትዩብ ገፁ ያስገኘውን ገንዘብ የመክፈያ መንገድ መሆኑን ጠቅሶ መቋረጡን የዘገበው ዋዜማ ሬዲዮ ነው። አንድ የዩትዩብ አካውንት ገንዘብ ለማስገኘት ሶስት መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት ይታወቃል። የመጀመሪያው ዩትዩብ ያስቀመጣቸውን ህግና መመሪያዎችን ማክበር ሁለተኛው ደግሞ የአድሰንስ አካውንት መክፈት ሲሆን ሦስተኛው የዩትዩብ ገፁ የሚጭናቸው ምስሎች የቅጂ መብቶችን ያከበሩ መሆን አለባቸው።

ሆኖም በዚህ ስዓት እነዚህን መስፈርቶች አሟልተው የሚሰሩና በኢትዮጽያ የሚገኙ ዩትዩበሮች የሰሩትን ገንዘብ ሳያገኙ 9 ቀናት ሆኗቸዋል ተብሏል።

የአድሰንስ የገንዘብ መክፈያ መንገድ በኢትዮጽያ ስራ ያቆመበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። ተመሳሳይ ችግሮችም በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች እንደተፈጠረም ተሰምቷል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe